loading
የአፍሪካ ሕብረት 40ኛው የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ የሕብረቱ አባል ሀገራት ሚኒስትሮችና የአህጉሩ ልዩ ልዩ ተቋማት ሃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ተጀምሯል፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሃማት በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግርበአህጉሩ በየአቅጣጫው እያጋጠመ ያለውን የሰላም እና ፀጥታ ችግር ለመፍታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶመስራት ይገባል ብለዋል፡፡ ሊቀመንበሩ የኮሮና ቫይረስ የፈጠረው ተፅዕኖ እና ለመቋቋም ስለሚደረጉ ጥረቶች፣ የአጀንዳ 2063የአፈጻጸም ሂደት፣ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና እና ሌሎች አህጉራዊ አጀንዳዎችንም አንስተዋል።የምክር ቤቱ ስብሰባ “የአፍሪካ አህጉርን […]

በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ ያደረሰው ጉዳት ወደ ሰው እንዳይሸጋገር እየተሰራ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከአጋር አካላት ጋር በመሆንድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ በሶማሌ ክልል 9 ዞኖችበተከሰተው የድርቅ አደጋ 960 ሺህ በላይ ዜጎች ተጎጂ በመሆናቸው የእለት ደራሽ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ በክልሉ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች የእለት ደራሽ ድጋፍ ይፈልጋሉ […]

እያንዳንዳቸው 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ቅጣት የተወሰነባቸው የንግድ ተቋማት…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 ግብይት ሳይኖር የደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የነበሩ 2 ድርጅቶችና 3 ግለሰቦች ከባድ የቅጣት ዉሳኔእደተላለፈባቸው ፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ቅጣቱ የተወሰነባቸው አባቢን ኮንስትራክሽን እና ማሽነሪ ኪራይ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እናዲን ጀነራል ትሬዲንግ የተባሉ ድርጅቶች መሆናቸውን ሚስቴሩ ገልጿል፡፡ ከንግድ ተቋማቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 3 ግለሰቦችም የገንዘብና የእስር ቅጣትተወስኖባቸዋል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡ አቶ ቢኒያም […]

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከአቶ ሙስጠፌ ሞሐመድ እና ከክልሉ ኃላፊዎች ጋር በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ተወያዩ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከአቶ ሙስጠፌ ሞሐመድ እና ከክልሉ ኃላፊዎች ጋር በአካባቢውበተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ተወያዩ። ፕሬዚዳንቷ ከ.ተ.መ.ድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ሞሐመድና የልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆንበሶማሌ ክልል ጉብኝት አድርገዋል። በቀብሪ በያ ባደረጉት የመስክ ጉብኝት በድርቁ የተነሳ ከተፈናቀሉት ወገኖች ጋር ተገናኝተዋል። የአካባቢው ሕዝብ ለተጎዱት ወገኖቹ የመጀመርያ ደራሽ በመሆን ላሳየው ታላቅነት እንዲሁም […]

ቡርኪናፋሶ ወታደራዊ አቃቤ ህግ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ብሌስ ኮምፓወሬ በ30 ዓመት እስር እዲቀጡ ጠየቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ አቃቤ ህግ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ብሌስ ኮምፓወሬ በ30 ዓመት እስር እዲቀጡ ጠየቀ፡፡ ኮምፓወሬ በሌሉበት ክስ የተመሰረተባቸው ከሳቸው በፊት ሀገሪቱን ሲመሩ በነበሩት ፕሬዚዳንት ቶማስ ሳናካራ ግድያ እጃቸው አለበት ተብለው ነው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደ ዘገበው እንደ አወሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1987 አብዮታዊው መሪ ቶማስ ሳንካራ መገደላቸውን ተከትሎ ወደ ስልጣን የመጡት ኮምፓወሬ ግድያውን ከጀርባ […]

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀገራችን ተቋማትን መገንባትና ለትውልድ ማሸገጋር እንደምትችል ማሳያ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀገራችን ተቋማትን መገንባትና ለትውልድ ማሸገጋር እንደምትችል ማሳያ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የባንኩን የ80ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓልና ያስገነባውን ዘመናዊ ህንፃ ማስመረቁን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ነው፡፡ ባንኩ ያስገነባውን ባለ 53 ወለል ህንፃ በሚያስመርቅበት ወቅት ተገኝተው ባደረጉት ንግግርም […]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ ከ96 በመቶ በላይ መድረሱን አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ ከ96 በመቶ በላይ መድረሱን አስታወቀ፡፡ኤጀንሲው መረጃውን ይፋ ያደረገው የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ኤጀንሲው የሳይበር ጥቃቶችን ቅድመ መከላከል፣ ጥቃት የደረሰባቸውን መልሶ ወደ ነበሩበት ስራ የመመለስ አቅሙ አድጓል ብለዋል። ባለፉት ስድስት ወራት ከሶስት ሺ […]

ቱርክ ምዕራባውያን ሀገራትት በዩክሬን ጉዳይ ሽብር የመንዛት ዘመቻቸውን ሊያቆሙ ይገባል ስትል አሳሰበች፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 ቱርክ ምዕራባውያን ሀገራትት በዩክሬን ጉዳይ ሽብር የመንዛት ዘመቻቸውን ሊያቆሙ ይገባል ስትል አሳሰበች፡፡ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ምዕራባውያን ሀገራት በዩክሬን ሁኔታ ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ መግለጫዎችን ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስተያየት የተሰማው ሩሲያ በዩክሬን ላይ በማንኛውም ጊዜ ጥቃት ልትፈፅም ትችላለች በማለት አሜሪካ ካስጠነቀቀች በኋላ ነው። እንዲህ ዓይነቱ […]

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሀገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሀገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳ፡፡ ምክር ቤቱ በስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ እንዲነሳ ወስኗል፡፡ ይህን ውሳኔ ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ […]

በክልሉ ሰላምን ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የሶማሌ ክልል አስታወቀ

በክልሉ ሰላምን ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የሶማሌ ክልል አስታወቀ፡፤ የሶማሌ ክልል መንግሥት ከሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በመሆን የክልሉን ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁንየክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል። በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በክልሉ ረብሻ፣ አለመረጋጋትና መንግስታዊ የኃላፊነት ቦታዎችን በኃይል ለመያዝ የተደረገ ሙከራ እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑንም […]