loading
የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ የፈፀመበት 84ኛው የሠማዕታት ቀን ታስቦ ዋለ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ የፈፀመበት 84ኛው የሠማዕታት ቀን ታስቦ ዋለ:: በአድዋ ሽንፈትን የተከናነበው የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር የዛሬ 84 ዓመት ዳግም ኢትዮጵያን ሲወር በአራቱም አቅጣጫ ይፋለሙት በነበሩ ኢትዮጵያዊያ ላይ ግፍና በደል ፈጽሟል። ግፍና በደሉን አንቀበልም ያሉት አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ግራዚያኒን በቦምብ ለመግደል ያደረጉትን ያልተሳካ ሙከራ ተከትሎም የግራዚያኒ […]

ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓት በሁሉም ሆስፒታሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓት በሁሉም ሆስፒታሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለፀ፡፡ ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ ሁሉም ሆስፒታሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ወ/ሮ አዳነች በየካቲት 12 ሆስፒታል በመገኘት ወረቀት አልባ ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓትን በይፋ ስራ አስጀምረዋል፡፡ በፕሮግራሙም ዛሬ የጀግኖች አርበኞች መታሰቢያ ቀን ለጀግኖች […]

በ5 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳደሮች ኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 በ5 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳደሮች ኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ:: በ5 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳድሮች ኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌዴራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ። እንደ ሀገር የስርጭት መጠኑ በወረርሽኝ ደረጃ ባይሆንም በጋምቤላ፣ አማራ፣ ሀረሪ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች፣ እንዲሁም በአዲስ […]

በዲሞክራቲክ ኮንጎ የጣሊያን አምባሳደር በጉዞ ላይ እያሉ በደረሰ የታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 16፣ 2013 በዲሞክራቲክ ኮንጎ የጣሊያን አምባሳደር በጉዞ ላይ እያሉ በደረሰ የታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸው ተሰማ:: አምባሳደር ሉካ አታናሲዮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተሸከርካሪ በሚጓዙበት ወቅት ነው ከግል ጠባቂያችው ጭምር ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትተው የተገደሉት፡፡ አምባሳደሩን እና አጃቢያቸውን ሲያጓጓዝ የነበረውና የሀገሬው ተወላጅ የሆነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድርጅት ሾፌርም በደረሰው ጥቃት ተገድሏል ነው የተባለው፡፡ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት […]

የናይጄሪያ ታጣቂ ቡድኖች አግተዋቸው የነበሩት 53 ሰዎችን ለቀቁ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 16፣ 2013 የናይጄሪያ ታጣቂ ቡድኖች አግተዋቸው የነበሩት 53 ሰዎችን ለቀቁ:: የሀገሪቱ ባለስልጣናት በሰጡት ማረጋገጫ ኒጀር ውስጥ በታጣቂዎቹ በእገታ ስር ከነበሩ ሰዎች መካከል 20 ሴቶችንና 9 ህፃናትን ጨምሮ 53ቱም ተለቀዋል፡፡ ሰዎቹ በታጣቂዎቹ ታፍነው የተወሰዱት ባለፈው ሳምንት በአውቶቡስ በሚጓዙበት ወቅት እንደነበር ተነግሯል፡፡ የኒጄር መንግስት ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ ታጋቾቹ በተቻለ ፍጥነት እንዲለቀቁ አስፈላጊው ድርድር ተደርጓል […]

ዲሞክራቲክ ኮንጎ በሀገሯ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ከመንግስ እውቅና ውጭ ከዋና ከተማዋ እንዳይወጡ ከለከለች፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 18፣ 2013 ዲሞክራቲክ ኮንጎ በሀገሯ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ከመንግስ እውቅና ውጭ ከዋና ከተማዋ እንዳይወጡ ከለከለች፡፡ ሀገሪቱ በዲፕሎማቶች ላይ ይህን እገዳ የጣለችው ሰሞኑን ለጉብኝት ከከተማ ውጭ ሲጓዙ የነበሩት የጣሊያኑ አምባሳደር መገደላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ማንኛውም የዲፕሎማቲክ ሚሽን አባላት ከዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ለመውጣት ሲፈልጉ ቀድመው ለመንግስት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ሺኬሴዲ ከዚህ […]

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በትራምፕ ዘመን የተጣለውን የግሪን ካርድ ክልከላ ህግ ሸረውታል::

አዲስ አበባ፣የካቲት 18፣ 2013 ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በትራምፕ ዘመን የተጣለውን የግሪን ካርድ ክልከላ ህግ ሸረውታል:: ትራምፕ 100 ሺህ 14 በሚል ድንጋጌ ያጸደቁት የቪዛ ክልከላ አዋጅ መነሻው የአሜሪካዊያንን የሥራ እድል ይጋፋል የሚል እንደሆነ ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ሆኖም አዲሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይህ አዋጅ አሜሪካን የሚጠቅም ሳይሆን የሚጎዳ ነው በማለት በፊርማቸው ሽረውታል፡፡ የባይደን አስተዳደር በዋናነት ህጉን የሻረበትን […]

ጂ አይ ዜድ እና ኦሬንጅ የኦሬንጅ በይነ መረብ ማዕከልን በኢትዮጵያ ከፈቱ፡፡

ጂ አይ ዜድ እና ኦሬንጅ የኦሬንጅ በይነ መረብ ማዕከልን በኢትዮጵያ ከፈቱ፡፡ ማዕከሉ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቃዊ አፍሪካ ሶስተኛውና ወጣቶችን በበይነ መረብ ቴክኖሎጂ ለማሠልጠንና የተሻለ የሥራ ዕድል እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ከዚህ ባለፈም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር የዲጂታል ክህሎትን የሚያጎለብትና ለልዩ ልዩ ፈጠራዎች የሚያነሳሳ የኦሬንጅ ዲጂታል ማዕከል […]

በአፍሪካ ለኮቪድ-19 ታካሚዎች ከፍተኛ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ እጥረት አለ ተባለ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 24፣ 2013 በአፍሪካ ለኮቪድ-19 ታካሚዎች ከፍተኛ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ እጥረት አለ ተባለ:: የኮሮናቫይረስ በአፍሪካ አህጉር ከተከሰተ ጀምሮ መካለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት አቅምን ያገናዘበ አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ እጥረት ትልቅ ፈተና መሆኑ ነው የሚነገረው፡፡ በአሁኑ ወቅት በታዳጊ ሀጋራት የሚገኙ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በየቀኑ የኦክስጅን ድጋፍ እንደሚፈልጉ አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስነብቧል፡፡ የኦክስጅን እጥረት በበርካታ […]

በናይጄሪያ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 25፣ 2013 በናይጄሪያ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ተሰማ:: ባለፈው ዓርብ በሰሜን ናይጄሪያ በአዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ እንዳሉ በታጣቂዎች ታግተው ተወስደው የነበሩ 279 ልጃገረዶች በሰላም ከወላጆቻቸው ጋር መቀላቀላቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ ልጃገረዶቹ ከአጋቾቻቸው እጅ ነፃ እዲወጡ የግዛቲቱ አስተዳዳሪዎች ሰፊ ድርድር አድርገው እንደነበር ነው የተነገረው፡፡ ታጋቾቹ ነፃ ከወጡ በኋላ የጤናቸው ሁኔታ በምርመራ […]