loading
ኮልፌ አጠና ተራ ታይዋን ሰፈር አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 ኮልፌ አጠና ተራ ታይዋን ሰፈር አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጸ:: አደጋው የደረሰው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታዉ ኮልፌ አጠና ተራ ታይዋን ሰፈር አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ትላንት ምሽት በደረሰው በዚህ የእሳት አደጋ 7 ሚሊዮን […]

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከደቡብ ክልል የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ዙሪያ በጂንካ ከተማ ምክክር እያካሄዱ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከደቡብ ክልል የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ዙሪያ በጂንካ ከተማ ምክክር እያካሄዱ ነው፡፡ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ፥ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በትምህርት ዘርፍ የገዘፈውን የጥራት መጓደል ለመፍታት ይሰራል። በኢትዮጵያ ለትምህርት ተደራሽነት የተሰጠውን ትኩረት ያህል ለጥራቱ ያለመጨነቅ ፣ የትምህርት ዘርፉ ከፖለቲካ ጋር […]

በ7 ቀናት ውስጥ 2 በመቶ የዩክሬን ዜጎች ተሰደዋል- ተ.መ.ድ በጦርነቱ ሳቢያ በ7 ቀናት ውስጥ 1 ሚሊዮን ዩክሬናዊያን ወደ ጎረበት ሀገራት መሰደዳቸው ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 በ7 ቀናት ውስጥ 2 በመቶ የዩክሬን ዜጎች ተሰደዋል- ተ.መ.ድ በጦርነቱ ሳቢያ በ7 ቀናት ውስጥ 1 ሚሊዮን ዩክሬናዊያን ወደ ጎረበት ሀገራት መሰደዳቸው ተሰማ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የዩክሬናዊያን ስደት በፍጥነቱ የክፍለ ዘመኑን ክብረ ወሰን ሊይይዝ እንደሚችል ያሳያል ብሏል፡፡ በቅርብ ቀናት ውስጥ ይህ ቁጥር ወደ 4 ሚሊዮን ከፍ […]

ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ‘ኤችአር 6600’ ረቂቅ ሕግን የሚቃወሙበት ሰልፍ በኒውጄርሲ ሊካሄድ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 ሰላማዊ ሰልፉ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም በአሜሪካ ኒውጄርሲ ግዛት እንደሚካሄድ የኒውዮርክ ኒውጄርሲ ተስፋ ለኢትዮጵያ ድርጅት ዋና ሰብሳቢ አቶ አክሊሉ ታፈሰ ለኢዜአ ገልጸዋል። ሕጉን ያረቀቁት የኒውጄርሲ የኮንግረስ አባል ቲም ማሊኖውስኪ በሚሰሩበት ቢሮ ፊት ለፊት እንደሚከናወንና እሳቸውንና ሕጉን የሚቃወሙ መልዕክቶች በሰልፉ ላይ እንደሚተላለፉ አመልክተዋል። ሕጉን በአሜሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት […]

በህገ ወጦች ላይ ምህረት የለሽ እርምጃ እንወስዳለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 በህገ ወጦች ላይ ምህረት የለሽ እርምጃ እንወስዳለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአቋራጭ ለመክበር በሚሞክሩ አካላት ላይ ምህረት የለሽ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋ በከተማዋ ዘይትን ጨምሮ በሌሎች ሸቀጦች ላይ ዋጋ የሚያስጨምር ምንም አይነት ምክንያት የለም በማለት ተናግረዋል፡፡ የምርት እጥረት ቢኖርም እንኳ ያለውን ምርት ግን በትክክል […]

ዩክሬን እና ሩሲያ ሶስተኛውን ዙር የሰላም ድርድር ለማካሄድ ተዘጋጅተዋል ተባለ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 ዩክሬን እና ሩሲያ ሶስተኛውን ዙር የሰላም ድርድር ለማካሄድ ተዘጋጅተዋል ተባለ። ለሁለት ሳምንታት ከሚጠጋ ጦርነት በኋላ ሁለቱ ሀገራት ለሦስተኛው ዙር ድርድር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት የልዑካን ቡድን አባላት ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በምዕራብ ቤላሩስ በሚገኘው ብሬስት ክልል የሁለት ዙር የሰላም ድርድር ላይ ሲሆን ከቀያቸው የሚፈናቀሉ […]

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በጦር ግንባር ጀብድ ፈፅመው ድል ላመጡ ሴቶች ምስጋና አቀረቡ::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ተከብሯል። ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በናንተ ድርብ መስዋዕትነት ሀገር ትቀጥላለችና ለናንተ ክብር መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የሀገራችን ሰላም በሴቶች ተጋድሎ ይረጋገጣል፤ በጀግና ሴቶች ሰማዕትነት ሀገራችን ታፍራ እና ተከብራ ትኖራለችም ብለዋል፡፡ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ […]

በሴት የሕክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የቀዶ ሕክምና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 በሴት የሕክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የቀዶ ሕክምና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ:: ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በሴት የሕክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ሰጠ፡፡ ሆስፒታሉ በሴት ሐኪሞች ብቻ በሚመራው በዚህ መርሀ ግብሩ ለ23 ያህል ሕሙማን ቀዶ ሕክምና እሰጣለሁ ብሏል፡፡ የሴቶች ሕክምና ቡድኑን የሚመሩት ዶ/ር መሰረት ሕይወቴ የቀዶ ሕክምና […]

ሱዳን በቀይ ባህር አካባቢ ሩሲያ የጦር ሰፈር እንድታቋቁም መፍቀዷ ግብፅን ቅር አሰኝቷል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 ሱዳን በቀይ ባህር አካባቢ ሩሲያ የጦር ሰፈር እንድታቋቁም መፍቀዷ ግብፅን ቅር አሰኝቷል ተባለ፡፡ የሱዳንን ሉዓላዊ ምክር ቤትን በምክትልነት የሚመሩት ጄኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ሞስኮ ደርሰው በተመለሱ ማግስት ሀገራቸው ለሩሲያ የጦር ሰፈር ግንባታ መፍቀዷን ይፋ አድርገዋል፡፡ዳጋሎ በመግለጫቸው ይህን በማድረጋችን ብሔራዊ ጥቅማችን እስካልተነካ ድረስ ስህተት የለውም የሚፈጥረው የፀጥታ ስጋትም የለም ብለዋል፡፡ የግብጽ […]

የመኪና ቀበኞችን በቁጥጥር አውያለሁ-የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 21 የመኪና ቀበኞችን በቁጥጥር አውያለሁ-የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን:: የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተሸከርካሪ ስርቆት ተሰማርተው የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውያለሁ አለ፡፡ በቡድን በመደራጀት እንዲሁም በተናጠል ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ እና ሲተባበሩ የነበሩ 21ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡ ቀደም ሲል ፈፃሚያቸው ያልታወቀ በሚል የተመዘገቡ የሥርቆት ወንጀሎች በእነዚህ ተጠርጣሪዎች […]