loading
2 ሺህ 921 የጤና ተቋማት ወድመዋል-የጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 በአሸባሪውቹ ህወሃት እና ሸኔ በአራት ክልሎች 2 ሺህ 921 የጤና ተቋማት መውደማቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጎማ ለፋና እንደተናገሩት በአማራ፣ አፋር ፣ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እና ኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች በሽብር ቡድኖቹ የጥፋት እጆች የጤናው ሴክተር ቀዳሚ ውድመት ደርሶበታል ብለዋል። በአማራ ክልል 40 ሆስፒታሎች፣ 450 ጤና ጣቢያዎች […]

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማራ እና አፋር ክልሎች የደረሱ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመቶችን ላጠና ነው አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት ጦርነት በነበረባቸው የአማራና አፋር ክልሎችና በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሰውን የሕይወትና የንብረት ውድመት በመስክ የሚያጠና ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ የጥናትና የምርምር ስራውን ጀምሯል። ከጥናትና ምርምር ቡድኑ የሚደርስበት ግኝት ውድመቱን ያደረሰውን አሸባሪ ቡድን የታሪክ ተወቃሽ በማድረግ በቀጣይ ለሚኖሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ይውላል ብለዋል። […]

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ “ዳያስፖራና ሀገር ግንባታ” በሚል ርእስ የዳያስፖራ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው።

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 የዳያስፖራ አባላቱ አሸባሪው ህወሃት በወረራ በቆየባቸው አካባቢዎች ያደረሰውን ጉዳትና ውድመት ለመጎብኘት ነው ትናንት አመሻሽ ወደ ስፍራው ያቀኑት፡፡ የዳያስፖራ አባላቱ ሰመራ ከተማ ሲገቡ በክልሉ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በዛሬው ዕለት የምክክር መድረክ ጀምረዋል። አሸባሪው ህወሃት በአፋር ክልል በትምህርት፣ በጤና እና በግብርና ዘርፎች ከ4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሷል […]

ምዕመናን የልደት በዓልን በቅዱስ ላልይበላ እንዲያከብሩ ጥሪ መቅረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 በልበ ሙሉነት የልደት በዓልን በቅዱስ ላልይበላ እንዲያከብሩ ጥሪ ቀረበ ጥሪውን ያስተላለፉት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ አብያተክርስቲያናትና ገዳማት አስተዳዳሪ አባ ፅጌ ሥላሴ መዝገቡ ናቸው፡፡ አካባቢው በችግር ውስጥ እንደነበር ያስታወሱት አባ ፅጌ ሥላሴ ሁላችንም በከባድ ሐዘን ውስጥ ነበርን፤ አሁን ግን ከወገናችን ጋር በዓሉን በተለመደው መልኩ ለማክበር ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡ የቤተክርስቲያኑ የተለመደው አገልግሎት ሳይጓደል […]

የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ ተፈጸመ:: ግዥው የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ከማስፍን አንጻር የዋጋ ግሽበትን የመቆጣጠርና የገበያ ዋጋን የማረጋጋት ፋይዳ እንዳለው የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ ሚኒስቴሩ ይህን የገለጸው የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የመቶ ቀናት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡ ባለፉት ጥቅምትና ህዳር ወራት የ4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ […]

የሠራዊቱን ስም ማጠልሸት በሀገር ላይ አደጋ ለመጣል መሞከር ነው-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሠራዊቱ ላይ አሉባልታ የሚነዙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቁ፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአገር መከላከያ ሠራዊት ከሌሎች የጸጥታ አከላት ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያ ላይ ተደቅኖ የነበረውን የህልውና አደጋ በመቀልበስ አኩሪ ገድል መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡ ሠራዊቱ የሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች አብራክ ክፋይና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የመጨረሻው […]

ጠ/ሚ ዐቢይ ከጆ ባይደን ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከጆ ባይደን ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት በዲፕሎማሲው አውድ መሻሻሎችየመኖራቸው ማሳያ ነው ሲል -የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት ከዚህ ቀደም የነበረውን የግንኙነት መንፈስ እየተቀየረ ለመሆኑ ማሳያ […]

ኑ ለኢትዮጵያና ስለድኻው ወገናችን ስንል ዝቅ እንበል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የሚቻለውን በቀለኝነት ትተን የማይቻለውን ይቅርታ እንዘምር ሲሉ መልእክት አስተላለፉ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የጥምቀትን በዓል አስመልክተው ለክርስትና እምነት ተከታዮች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸው ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ መልእክታቸው ፍቅራችንን፣ ትህትናችንንና ክብራችንን ለሀገራችንና ለወገናችን እናሳይ፣ በተለመደው መንገድ ብቻ ሄደን ሀገራችንን እንደማናድናት እንገንዘብ ብለዋል። ኑ ለኢትዮጵያና ስለድኻው […]

በታላቁ ቤተ-መንግሥት የዕራት መርሐ-ግብር ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 በታላቁ ቤተ-መንግሥት የዕራት መርሐ-ግብር ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡ በታላቁ ቤተ-መንግሥት በተካሄደው የዕራት መርሐ-ግብር ከትኬት ሽያጭ በቀጥታ ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ። በመርሐ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዳያስፖራ አደረጃጀት መሪዎች፣ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር […]

ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ከክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ከሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል አንዱ የሚገኝበትን ቀብሪበያን […]