loading
ትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ከመደበችው በጀት 40 በመቶውን ለክትባት ታውላለች አሉ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 ኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ከመደበችው በጀት 40 በመቶውን ለክትባት ታውላለች አሉ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፡፡ ፕሬዝደንቷ ይህን ያሉት የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በጠሩት ዓለም አቀፍ የክትባት ጉባኤ ላይ ላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ከመደበችው በጀት መካከል በዚህ መጠን ለማዋል መነሳቷ መንግስት ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት መስጠቱን እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡ የበርካታ ሀገራትና መንግሥታት […]

ይህን ክፉ ጊዜ ያለው ለሌለው በማጋራት በመተጋገዝ ልናልፈው ይገባል-አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 ይህን ክፉ ጊዜ ያለው ለሌለው በማጋራት በመተጋገዝ ልናልፈው ይገባል-አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፡፡ ይህን ክፉ ጊዜ ለማለፍ እርሾ ለሚያጥራቸው ጎረቤቶች ያለው ለሌለው በማጋራት ማለፍ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ጥሪ አቅርበዋል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመኖሪያ አካካቢያቸው ለሚገኙ ከ114 በላይ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የተለያዩ ምግብ ነክ ድጋፎችን አበርክተዋል።  አቶ […]

የአልቃይዳ የሰሜን አፍሪካ መሪ አብደልማሌክ ድሩክደል በፈረንሳይ ጦር ተገደሉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 የአልቃይዳ የሰሜን አፍሪካ መሪ አብደልማሌክ ድሩክደል በፈረንሳይ ጦር ተገደሉ፡፡ የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አብደልማሌክ ድሩክደል በሰሜናዊ ማሊ ግዛት በፈረንሳይ ወታደሮች መገደሉን አስታውቋል፡፡ እንደ አልጄዚራ ዘገባ የሰሜን አፍሪካ የአለቃይዳ አዛዥ በማሊ ለሰባት ዓመታት በፈረንሳይ ወታደሮች ሲታደን መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በሽብረተኛ ቡድን መሪው መገደል ዙሪያ ከአልቃይዳ በኩል ምንም የተባለ ነገር […]

ቦልሶናሮ የዓለም ጤና ድርጅትን ጥለው ሊወጡ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 ቦልሶናሮ የዓለም ጤና ድርጅትን ጥለው ሊወጡ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ ::የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ዣየር ቦልሶናሮ አሜሪካን ተከትለን ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነታች ለመውጣት ሁኔታውን ያእጠናነው ነው ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት የሀገራት መሪዎች ተጥለው የነበሩ የእንቅስቃሴ እገዳዎችን ለማንሳት መጣደፍ እንደሌለባቸው ማስጠንቀቁን ተከትሎ ነው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ ድርጅቱ በፖለቲካዊ አድልዎ ምክንያት ሁሉንም ሀገራት […]

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ። መርሀግብሩ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አርሶአደሮች መንደር ላይ ነው የተጀመረው።ኢ/ር ታከለ ኡማ ከግብርና ሚንስትሩ ዑመር ሁሴን ጋር በጋራ በመሆን መርሀግብሩን አስጀምረዋል። በዛሬው እለትም የከተማው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አርሶ አደሮች ማሳ ላይ በመገኘት አርሶአደሮቹን ያገዙ ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎችም ችግኝ ተክለዋል። ኢ/ር ታከለ ኡማ የዘንድሮው የበጎ ፈቃድ መርሀግብር አዋሳኝ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ለፍልስጤማዊው ወጣት ሞት ይቅርታ ጠየቁ ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ለፍልስጤማዊው ወጣት ሞት ይቅርታ ጠየቁ :: የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታያሁ ለወጣቱ እናት የይቅርታ መልእክታቸውን ያተላለፉት ከተገደለ አንድ ሳምንት ካለፈው በኋላ ነው፡፡ እየሩሳሌም ውስጥ በእስራኤል ፖሊሶች የተገደለው የ32 ዓመቱ ወጣት ኢያድ ሀላክ ከልጅነቱ ጀምሮ የኦቲዝም ታማሚ ነበር ተብሏል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ኔታኒያሁ በሰጡት መግለጫ […]

ኒው ዚላንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ አለማስመዝገቧን ተከትሎ ክልከላዎችን በሙሉ ልታነሳ ነው ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 ኒው ዚላንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ አለማስመዝገቧን ተከትሎ ክልከላዎችን በሙሉ ልታነሳ ነው ::የኒው ዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደን በሀገራቸው ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች እንዴሌሉ ተናግረው ከእንግዲህ አካላዊ መራራቅን እንጅ እንቅስቃሴን አንገድብም ብለዋል፡፡ ይሁን እንጅ ከውጭ የሚገቡ ዜጎቻችን ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ ማድረግ የግድ ይላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሯ ለተገኘው ውጤት ሁሉንም ዜጎቻቸውን […]

ግብፅ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 47 ዶክተሮቿን በሞት ማጣቷ ትልቅ ስጋት ሆኖባታል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2 ፣ 2012 ግብፅ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 47 ዶክተሮቿን በሞት ማጣቷ ትልቅ ስጋት ሆኖባታል ተባለ::የብግብፅ የህክምና ማህበር በሰጠው መግለጫ የሀገሪቱ የጤና አጠባበቅ ስርዓት በፍጥነት ካልተስተካከለና ለሀኪሞች ልዩ እንክብካቤ ካልተደረገላቸው የበለጠ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ብቻ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሰባት ዶክተሮች መሞታቸው ሁኔታው ምን ያህል አደገኛ እየሆነ መምጣቱን ያሳያል ነው የተባለው፡፡ ከሁለት […]

ኬንያዊያን ፖሊስ በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን ግድያ ያቁም የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ነው::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2 ፣ 2012 ኬንያዊያን ፖሊስ በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን ግድያ ያቁም የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ነው:: በኬንያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የተጣለውን የእንቅስቃሴ እገዳ ተከትሎ ፖሊስ ህግ በማስከበር ሰበብ በርካታ የሰብዓዊ መብቶችን እየጣሰ እንደሆነ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰዎች ተናግረዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው መንግስት እገዳውን ከጣለ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በፖሊስና በነዋሪዎች መካከል በተከሰቱ ግጭቶች ከ15 ያላነሱ […]

የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በልብ ህመም በድገንገት ህይዎታቸው አለፈ ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3 ፣ 2012የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በልብ ህመም በድገንገት ህይዎታቸው አለፈ ::የብሩንዲ መንግስት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ፕሬዚዳንቱ በልብ ህመም መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ቅዳሜ በአንድ የቮሊቦል ጨዋታ ውድድር ላይ ታድመው የነበረ ሲሆን በዚያው ምሽት ታመው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ የጤናቸው ሁኔታ መሻሻል አሳይቶ የነበረ ቢሆንም ሰኞ እለት በተደረገላቸው […]