loading
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚያካሄድ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ዶክተር ታቦር ገብረ መድህን ገለጹ።

አፈ ጉባኤው ዶክተር ታቦር እንዳሉት ምክር ቤቱ ዛሬ ሰባት ሰዓት በሚያካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ከሚመለከታቸው አጀንዳዎች መካከል አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትን ማጽደቅ እና ምክር ቤቱ በወረዳ ደረጃ የሚገኙ አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀትን የሚመለከት አዋጅም መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል አፈ ጉባኤ።

የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳልህ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ።

የኤርትሪያን ፕሬስ እንደዘገበዉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኢፌዴሪ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጉብኝቱ ዳግም የተጀመረውን የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንደሚያግዝም ታምኖበታል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ለ20 አመታት አቋርጠውት የነበረውን ግንኙነት ዳግም መጀመራቸው ይታወሳል። በቅርቡም የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከኤርትራው […]

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጀዋር ሙሃመድ ዛሬ በባሕር ዳር ከሚገኙ ወጣቶች እና አክቲቪስቶች ጋር በአቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል ይወያያል።

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጀዋር ሙሃመድ ዛሬ በባሕር ዳር ከሚገኙ ወጣቶች እና አክቲቪስቶች ጋር በአቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል ይወያያል። ከጃዋር ጋር ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳን ጨምሮ ከኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የተገኙ ልዑካንም የሚሳተፉ ሲሆን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ አስር ግለሰቦች ከጎንደር እንዲሚገኙ ታውቋል።

አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ፖለቲካ ትግሉ ልንመጣ የምንችለው ያፈረሰን የምርጫ ቦርድ እራሱ ከፈረሰ ብቻ ነው አሉ፡፡

ፓርቲ ከሌለኝ በግለሰብ ደረጃ የማደርገው ተሳትፎ ብዙም ጥቅም ይኖረዋል ብዬ አላስብም ብለዋል ለቢቢሲ፡፤ መቀሌ ተዘጋጅቶ በነበረ ጉባኤ መሳተፋቸው ያላስደሰታቸው ወገኖች ዛቻና ማስፈራሪያ እንዳደረሱባቸውና ይህም ለውሳኔ እንዳበቃቸው ተናግረዋል። ለምን መቀሌ ሄዶ ስብሰባ ተካፈለ ብለው ከፍተኛ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተውብኝ፤ እንገድልሃለን፤ ንብረትሀን እናቃጥላለን የሚሉ መልእክቶች እየደረሱኝ ነው ብለዋል። በድርጅት ደረጃ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ እስከሌለ ድረስ፤ ነጻ ሐሳባቸውን […]

የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) በሚቀጥሉት ሶስተ ቀናት ውስጥ ወደ ኢትዮጲያ ገብቶ ስራ ይጀምራል ተባለ::

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ወደአዲስ አበባ ልዑካን እንደሚያሰማራ እና ጽሕፈት ቤቱን ከፍቶ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንደሚጀምር የድርጅቱ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ለ ቪ ኦ ኤ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጲያ መንግስትም በአስመራ ከሚገኘው የ ኦነግ ድርጅት ጋር በኢትዮጲያ ይልቁንም በኦሮሚያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዴት ህዝቡን ባሳተፈ መልኩፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው ከስምምነት መድረሳቸው ነው የተነገረው፡፡ አቶ ዳውድ ድርጅታቸው […]

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ አዲስ ካቢኔ ለምክር ቤቱ አዳዲስ የካቢኔ አባሎቻቸውን አቅርበዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ አዲስ ካቢኔ ለምክር ቤቱ አዳዲስ የካቢኔ አባሎቻቸውን አቅርበዋል፡፡ ወ/ሮ አልማዝ አብርሃ የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ተፈራ የፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጀማሉ ጀምበር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ ለገቢዎች ሃላፊ ዶ/ር ፍሬህይወት ገ/ህይወት ለፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊነት አቶ አሰፋ ዪሃንስ ለቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ኤርምያስ ለኢንደስትሪ ቢሮ […]

አቡዳቢ ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ልትዘረጋ ነው ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሪም አል ሃሺሚ አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተው በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል። ሚድል ኢስት ሞኒተር የኢትዮጵያ የስራ ኃላፊዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሩ ከአዲስ አበባ አሰብ ይዘረጋል ። የጠቅላይ ሚንስትሩ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አርጋ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ከአቡዳቢ ጋር የተደረገው ውይይት በኢንቨስትመንት፣በግብርናና በሌሎች ዘርፎች […]

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዩስን መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመሄድ ጎበኙዋቸው፡፡

በጉብኝቱ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ተገኝተዋል፡፡ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩም እንዳሉት አቡነ መርቆርዮስን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሆን በመጎብኘታቸው ከፍ ያለ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከአቡነ መርቆርዮስ ጋር ስለይቅርባይነትና ስለፍቅር ተወያይተዋል፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጠቅላይ ሚኒስተሩ አቡነ መርቆርዮስን መኖሪያ ቤታቸው ድረስ ተገኝተው በመጎብኘታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ባለፉት 26 ዓመታት […]