loading
ህንድ ህዝቤን ያስጨነቁ ሰው በሊታ ነብሮችን ገደልኩ አለች

አርትስ 27/02/2011

በሳምንቱ መጀመሪያ የተሰማውንና “ህንድ ህዝቤን በፍርሃት ያስጨነቁ ሁለት ሰው በሊታ ነብሮችን ገደልኩ አለች” የሚለውን ወሬ ታዋቂዎቹ ኒውዮርክ ታይምስ፣ፎክስ ኒውስ እና አሶሺየትድ ፕሬስ ተቀባብለው ዘግበውታል።

ለአራት ጊዜ ያህል የተካሄደባቸውን ጠንካራ ከበባ ሰብረው ያመለጡት ሁለቱ ነብሮች በተለያየ አካባቢ የሚኖሩ ቢሆንም በሃገሪቱ እጅግ አደገኛ ናቸው ተብለው ለግድያ ሲፈለጉ የነበሩ ናቸው ብለዋል የህንድ ባለስልጣናት። በጥብቅ ደን አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችም  ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ቆይተዋል ተብሏል። የህንድ ፖሊስ ነብሮቹ እንዲገደሉ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ዘመቻ ተጀምሯል።

በሁለት አመት ብቻ 13 ሰዎችን መብላቷ የተነገረላት በምዕራባዊ ማሃራሽትራ ግዛት የምትገኘው አንደኛዋ ነብር በተደጋጋሚ ጊዜ የተደገሰላትን ሞት ብታመልጥም  ባለፈው አርብ ግን ድንገት በምትኖርበት ጫካ ውስጥ እንዳለች  በትራክተር ተገጭታ ተገድላለች።

ዱብሃዋ በተባለ ጥብቅ ደን ውስጥ ትኖርየነበረችውና ተመሳሳይ አደጋ በማድረስ አደገኝነቷ የተወራላት ነብርም ከዚህ እጣ አላመለጠችም።

አልሞ ተኳሾችንና ስልጡን ዝሆኖችን በማካተት በመንግስት ሃይሎችና በአካባቢው ነዋሪዎች የተካሄደው አሰሳ  በወታደራዊ ዘመቻ ደረጃ የተቀነባበረ ነበርይላል ጋዜጣው ።

ነብሯን ከተደበቀችበት ስፍራ ለማውጣት የአካባቢው የደን ሃላፊዎች የፈጠሩት መላም ብዙዎችን አስደንቋል። የኬልቪን ክሌይን ኮሎኝ ከነብር ሽንት ጋር በማደባለቅ ወደነብሯ ዋሻ ውስጥ መንፋት ነበር ዘዴው። ከሰዓታት በኋላ በዚያ መጥፎ ጠረን አቅሏን የሳተችው ነብር ከዋሻዋ ወጥታ መሮጥ ስትጀምር አልሞ ተኳሾች ባነጣጠሩባት ጥይት ተመትታ ወደቀች፣ እዛው ላይ ሞተች ብሏል ጋዜጣው።

“አሁን በህንድ ጥብቅ ጫካ አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች በደስታ እፎይ ብለዋል” ብሏል አሶሺየትድ ፕሬስ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *