ለካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ ሀገራት ትኬታቸውን እቆረጡ ነው
አርትስ ስፖርት 10/03/2011
በመጭው የፈረንጆች ዓመት በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በርካታ ሀገራት ተሳታፊነታቸውን እያረጋገጡ ነው፡፡
ትናንት ምድብ I ኑኮት ላይ ሞሪታኒያ ቦትስዋናን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በመርታት በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የምታቀና ይሆናል፡፡ በምድቡ አንጎላ ቡርኪና ፋሶን በተመሳሳይ 2 ለ 1 ረትታለች፡፡ በምድብ H ኮናክሪ ላይ ጊኒ ከ አይቮሪ ኮስት አንድ አቻ ቢለያዩም፤ ተያይዘው ወደ ቀጣዩ ዓመት ውድድር ተሳፊነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ሩዋንዳ ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ሁለት አቻአጠናቅቀዋል፡፡
በምድብ K ዛምቢያ ደግሞ በሞዛምቢክ የ1 ለ 0 ሽንፈት ማስተናገዷን ተከትሎ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ውጭ ሆናለች፡፡ ቅዳሜ እዚሁ ምድብ ጊኒ ቢሳው እና ናሚቢያ ያለ ግብ አቻ መለያየታቸውንተከትሎ ከምድቡ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታ ይጠብቃሉ፡፡ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ F ጋና ዋልያዎቹን 2 ለ 0 ስትረታ ኬንያና ጋና የማለፍ ዕድል አላቸው፡፡
በምድብ L ሌሴቶ ታንዛንያን፤ ዩጋንዳ ኬፕ ቨርዴን በተመሳሳይ 1 ለ 0 ሲያሸንፉ ዩጋንዳ ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማቅናታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ምድብ A ላይ አስቀድማ ማለፏንያረጋገጠችው ማዳጋስካር በሱዳን የ3 ለ 1 ሽንፈት ገጥሟታል፤ ከምድብ D አልጀሪያ ቶጎን 4 ለ 1 በመርታት የካሜሮን ትኬቷን ቆርጣለች፡፡ በምድብ J ደግሞ ኒጀር ኢስዋቲኒን 2 ለ 1 ስትረታ፤ ግብፅናቱኒዚያ ምድቡ ላይ ማለፍ ችለዋል፡፡ ናይጀሪያ፣ሴኔጋል፣ማሊ፣ሞሮኮ እና ካሜሮን በአስተናጋጅት ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡