loading
ለጋሽ ድርጅቶች ለቤተሰብ ምጣኔ የ350 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ

አርትስ 05/03/2011

የድጋፍ ገንዘቡ ቃል የተገባው ሩዋንዳ ኪጋሊ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው የ2018 ዓለምአቀፍ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት  ጉባዔ ላይ ነው።

መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው ግሎባል ሄልዝ ስትራተጂስ ለአርትስ ቲቪ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው በለጋሽ ድርጅቶቹ ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 260 ሚሊዮን ዶላር የተገኘው ከእንግሊዝ የልማት ትብብር መስሪያ ቤት ሲሆን ቀሪው 78 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከካናዳ ዓለምአቀፍ ትብብር የተለገሰ ነው።18 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ደግሞ ከሜሊንዳ ኤንድ ጌትስ ፋውንዴሽን የተለገሰ ነው።

የድጋፍ ገንዘቡ በደሃ ሃገራት ለሚገኙ 3 ሚሊዮን ጥንዶች የሁሉን አቀፍ ጤናማ ጾታዊ ህይወት ፕሮግራም ማበልጸጊያና ለስነተዋልዶ ጤና መብቶች አጠባበቅ ፕሮግራሞች ማስፋፊያ ይውላል ተብሏል ።

ከተለያዩ ሃገራት የተውጣጡ 3ሺህ 700 ተወካዮች ተሳታፊ በሆኑበት በዚሁ ጉባዔ ላይ  ንግግር ያደረጉ  መሪዎች በደሃ ሃገራት ለሚካሄዱ የቤተሰብ ምጣኔ ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የሩዋንዳ የፋይናንስ እና የኢኮኖሚ ሚኒስትር ዶክተር ዑዜይል ዳጊጂማና  በጉባዔው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት መስፋፋት በጤና፣ በትምህርት፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው ።

ከግማሽ በላይ የሆነው የዓለም ህዝብ ወጣት ሲሆን ከዚህም ውስጥ 1.2 ቢሊዮን የሚሆነው የሚኖረው በታዳጊ ሃገራት ነው። በጉባዔው ላይ አጽንዖት የተሰጠውም ይኸው ወጣቶችን በቤተሰብ ዕቅድ ፕሮግራም ተደራሽ ማድረግ ለታዳጊ ሃገራት በሚኖረው ፋይዳ ላይ ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *