loading
መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማስጠበቅ ልሲ ኦነግን ትጥቅ የማስፈታቱን ስራ እሰራለሁ አለ

አርትስ30/01/2011
ኦነግ ወደ ሀገር የገባው ትጥቅ ፈትቶ ነው አሁንም ቢሆን የቀረውን ትጥቅ መፍታት አለበት፤ ካልሆነ ግን መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማስጠበቅ ሲል ኦነግን ትጥቅ የማስፈታቱን ስራ እንደሚሰራ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡
መንግስት መግለጫዉን የሰጠዉ ከሰሞኑ የኦነግ አመራር አቶ ዳኦድ ኢብሳ ከዋልታ ቴቪ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ከመንግስት ትጥቅ ለመፍታት አልተደራደርንም ፤ትጥቅ የሚፈታም የሚያስፈታም የለም ማለታቸዉን ተከትሎ ነዉ ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *