loading
ሜሪካ የግብፁን ሙስሊም ወንድማማቾች ህብረት  ድርጅት በአሸባሪነት  ልትፈርጅ ነው፡፡

አሜሪካ የግብፁን ሙስሊም ወንድማማቾች ህብረት  ድርጅት በአሸባሪነት  ልትፈርጅ ነው፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት ይህ ድርጅት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀ በድርጅቱና በአባላቱ ላይ የጉዞና የኢኮኖሚ ማእቀቦች ይጣሉበታል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው አሜሪካ ሙስሊም ወንድማማቾችን በአሸባሪነት መዝገብ ውስጥ ለማስፈር  የወሰነችው ከሶስት ሳምንታት በፊት የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል ሲሲ አሜሪካን  መጎብኘታቸውን ተከትሎ ነው።

ሮይተርስ በዘገባው  ዶናልድ ትራምፕ ይህን እንዲያደርጉ አል ሲሲ ጠይቀዋቸዋል ሲል አስነብቧል።

ትራምፕና አል ሲሲ መገናኘታቸውን ተከትሎ ትራምፕ ወዲያው ሙስሊም ብራዘርሁድ ላይ የኢኮኖሚ ማእቀብ መጣል የሚቻልበትን መንገድ እንዲፈልጉ የደህንነትና የዲፕሎማሲ አማካሪዎቻቸውን ማዘዛቸውንም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

ትናንት የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ሳራ ሳንደርስ የትራምፕ አስተዳደር በውሳኔው እየገፋበት እንደሆነ አስታውቀዋል።

ሳንደርስ በመግለጫቸው ፕሬዝዳንቱ ከደህንነት አማካሪዎቻቸው እንዲሁም ከአካባቢው መሪዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ተወያይተዋል፣ እናም ይህ ውሳኔ በዛው መሰረት እየተኬደበት ያለ ነገር ነው ብለዋል፡፡

የኒዮርክ ታይምስ ዘገባ  ደግሞ ውሳኔው በዋይት ሃውስ ባለስልጣናት እና በፔንታጎን ሃላፊዎች መካከል አለመግባባት ፈጥሯል ይላል።

ሙስሊም ወንድማማቾች ዋይት ሃውስ ምንም ይበል ምን በዓላማው ፀንቶ እንደሚቀጥል በድረ ገፁ ላይ ማስፈሩንም ሮይተርስ ዘግቧል።

ሰላም ገብሩ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *