loading
ሞሪንሆ በታክስ ስወራ ወንጀል የተወሰነበትን ፍርድ በፀጋ ተቀብሏል

ሞሪንሆ በታክስ ስወራ ወንጀል የተወሰነበትን ፍርድ በፀጋ ተቀብሏል

 

ዦዜ ሞሪንሆ በስፔን ፍርድ ቤት በተከፈተባቸው የታክስ ማጭበርበር ክስ የፍርድ ውሳኔ ተሰምቷል፡፡

በውሳኔው ሞሪንሆ የአንድ ዓመት እስራት ተበይኖበታል፡፡ የእስር ውሳኔ ይተላለፍባቸው እንጂ ተፈፃሚ አይሆንም ተብሏል፤ ከዛ ይልቅ በ182.500 ዮሮ አሊያም በ160.160 ፓውንድ ተቀይሮ ገንዘቡን ገቢ ያደርጋል ተብሏል፡፡

በስፔን አንድ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰሰ እንደሆነና ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ እስር ቢፈረድበት በገንዘብ መቀየር ይችላል፡፡

ሞሪንሆም ከ2011- 2012 በሪያል ማድሪድ አሰልጣኝነት በነበረው ቆይታ ከስፔን የታክስ ባለስልጣን የ3.3 ሚሊዮን ዩሮ የታክስ ስወራ አድርሰሃል ተብሎ ተጠይቋል፡፡

አቅቢ ህግ አሰልጣኙ የቢዘነስ እንቅስቃሴውን በተለያዩ አካላት ማሰራቱ እንዲሁም በነዚህም አካላት ሆነ ተብሎ የታክስ ስወራ ለመፈፀም ደባ እንደተሰራ ተናግሯል፡፡

በቅርቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በታክስ ማጭበርበር የቅጣት ውሳኔ እንደተላለፈበት ይታወቃል፡፡ ከዚያ በፊት ደግሞ ዣቪ አሎንሶ፣ ማርሴሎ፣ ሊዮኔል ሜሲ እና ኔይማር ላይ በተከፈተ ተመሳሳይ ክስ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *