loading
ረሺዳ ትሌይብ እና ኢልሀም ኦማር በሚቺጋንና በሚኒሶታ ታሪክ ሰሩ

ረሺዳ ትሌይብ እና ኢልሀም ኦማር በሚቺጋንና በሚኒሶታ ታሪክ ሰሩ

አርትስ 28/02/2011

በአሜሪካ ኮንግረስ ታሪክ እነዚህ ሁለት ሙስሊም ሴቶች የመጀመሪያዎቹ ተመራጮች በመሆን ነው አዲስ ታሪክ ያስመዘገቡት፡፡

የዘር ሀረጋቸው ከፍልስጤም የሚዘዘው ረሺዳ ትሌይብ እና ከምስራቅ አፍሪካዋ ሶማሊያ  የተገኙት ኢልሀም ኦማር በአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ የዴሞክራት ፓርቲን ወክለው ነው  ያሸነፉት፡፡

 የፖለቲካል ሳይንስ እና የህግ ምሩቋ  ትሌይብ ሚቺጋን 13ኛው ዲስትሪክት የምክር ቤት መቀመጫ ሲያሸንፉ ኦማር ደግሞ ለሚኒሶታ 5ኛው ዲስትሪክት ተወዳድረው ነው የምክር ቤት ወንበር ማሸነፍ የቻሉት፡፡

ከአሁን በፊት ይህ ለሙስሊም ሴቶች የማይቻል ተደርጎ ይታሰብ ነበር ያሉት ትሌይብ አሁን እንዴት እንደሚቻል እኛ አሳይተናል፣ ሌሎችም ነገ ይደግሙታል ብለዋል፡፡

ትሌይብ በቲውተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለምን ተወዳደርሽ ለሚሉኝ ሰዎች መልሴ ፕሬዝዳንቱ ሲሳሳቱ ዳኝነት ለመስጠት ትክክለኛዋ ሰው ነኝ ብየ ስለማምን ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ምርጫ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበርን ዴሞክራቶች በአብልጫ ድምፅ ሲያሸንፉ ሪፐብሊኮቹ ደግሞ የሴኔቱን መቀመጫ  ተቆጣጥረውታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *