ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረገፆች ሲሰራጩ የነበሩ በርሃብ ክፉኛ የተጎዱ ሕጻናት እና ወላጆችን የሚያሳዩ ምስሎች የጌዲዮ ተወላጆች ምስል መሆናቸው ተረጋገጠ
ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረገፆች ሲሰራጩ የነበሩ በርሃብ ክፉኛ የተጎዱ ሕጻናት እና ወላጆችን የሚያሳዩ ምስሎች የጌዲዮ ተወላጆች ምስል መሆናቸው ተረጋገጠ ፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበርም ከኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ የተፈናቀሉት ለሞት የሚያሰጋ ረሃብ የጠናባቸው መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ሲል ለሸገር ራዲዮ ተናግሯል፡፡
አረትስ ቴሌቪዠን ከብሄራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው የስልክ ግንኙነት በብሄራዊ አደጋ እና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአቅርቦት እና ሎጂስቲክስ ዳይሬክተር አቶ አይድሩስ ሁሴን ተቋሙ ለሞት የሚያበቃ የምግብ ዕጥረት ስለመከሰቱ መረጃ እንደሌለው ነግረውናል፡፡
ኮሚሽን መስሪያቤቱ እስከአሁን ለተፈናቃዮች ድጋፍ ያላደረገው የክልሉ መንግስት የድጋፍ ጥያቄ ባለማቅረቡ ነው በማለት በተለይም ኮሚሽኑ በማህበራዊ ድረገፆች የተሰራጩትን ፎቶዎች እና መረጃዎች የሚያጣራ ቡድን በቦታው መላኩን አስመልክቶ የሰጠውን መረጃ አርትስ ቴሌቪዠን ዘግቦ እንደነበር አይዘነጋም።
ኮሚሽን መስሪያቤቱ ለጊዜው ምስሎቹ ተፈናቃዮች ሃይል ሰጪ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው የሚያሳዩ በመሆናቸው ሁለት መቶ ኩንታል ሃይል ሰጪ ብስኩቶች፣ ሲ ኤስ ቢ ፕላስ የሚባሉ አልሚ የምግብ አይነቶችን፣ አተር ክክ እና ዘይት ወደ ቦታው መላኩንም ተናግሮ ነበር።
ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረገፆች ሲሰራጩ የነበሩና በርሃብ ክፉኛ የተጎዱ ሕጻናት እና ወላጆችን የሚያሳዩ ምስሎች የጌዲዮ ተወላጆች ምስል መሆናቸውን ከቀይ መስቀል እና ሌሎች አካላት መረጋገጡ ተነግሯል፡፡
ተፈናቃዮቹ በዋናነት ድጋፍ እያገኙያሉት በኤን ጂኦዎች ጥምረት መሆኑን አርትስ ለማወቅ ችሏል፡፡
በመሆኑም ከቀያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ ከጊዜአዊ ድጋፍ ባለፈ ዘላቂ መፍትሄ የሚያሻው ነው፡፡