loading
ሰብዓዊ መብት የምናከብረውና የምናስከብረው ለማንም ብለን ሳይሆን ለህዝባችንና ለፍትህ ስንል አሉ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ::

ሰብዓዊ መብት የምናከብረውና የምናስከብረው ለማንም ብለን ሳይሆን ለህዝባችንና ለፍትህ ስንል አሉ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ::
“ሰብዓዊ መብት የምናከብረውና የምናስከብረው ለማንም ብለን ሳይሆን ለህዝባችንና ለፍትህ ስንል ነው” ሲሉ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ሰሞኑን አመነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ላይ ይዞ በወጣው ሪፖርት ዙሪያ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ “በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የወጣውን መግለጫ ተመልክተነዋል፤ የማጣራት ስራም ጀምረናል” ብለዋል።“የማጣራት ስራችንን አጠናቀን ምላሽ ለመስጠት በሂደት እያለን መግለጫው በተለያዩ ሚዲያ ተሰራጭቷል” ሲሉም ጠቅሰዋል። “አሁንም ቢሆን ዘገባውን ከይዘቱ፣ ከአካሄዱ፣ እንዲሁም የጉዳዩን እውነተኛነት እና ገለልተኛነት የማጣራት ስራችንን በቶሎ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው” ሲሉም ገልፀዋል።“በማጣራት ስራችን በሚገኘውም ውጤት፣ ሪፖርቱ እውነት በሆነበት ልክ፣ መወሰድ ያለበቸውን እርምጃዎች እንወስዳለን” ብለዋል ወይዘሮ አዳነች በመልእክታቸው።ሀሰት በሆነበት ወይም በተጋነነበት አኳያ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል ጋራ በመወያየት ሪፖርቱ እንዲስተካከል ለማድረግ እንደሚጥሩ በመግለፅ፤ “ይህ ባይቻል እንኳን ህዝቡ እና አለም ዓአፉ ማህበረሰብ እውነቱን እንዲያውቀው በመረጃ አስደግፈን እናሳያለን” ሲሉም አስታውቀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *