በህንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ክብረ ወሰን የሆነ የኮሮናቫይረስ ሞት ተመዘገበ::
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11፣ 2013 በህንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ክብረ ወሰን የሆነ የኮሮናቫይረስ ሞት ተመዘገበ
በህንድ እየተባባሰ የመጣውን የኮሮናባይረስ ወረርሽኝ መቆጣጠር ያቃታቸው ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በህዝባቸው ዘንድ የነበራቸውን አመኔታ ዝቅ እንዲል አድርጎባቸዋል፡፡
በ24 ሰዓታት ውስጥ 4 ሽህ 529 ዜጎቿን በቫይረሱ የተነጠቀቸው ህንድ አሁንም በወረርሽኙ ጠንካራ ክንድ እየተደቆሰች ትገኛለች፡፡በየቀኑ በአማካይ ከ250 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 የሚያዙባት ይህች ሀገር በድምሩ ከ25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወረርሽኙ የተያዙባት ሲሆን ይህም ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ አስተዳደር ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚያደርገው ጥረት አናሳ ነው የሚል እምነት ያላቸው አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ከእንግዲህ የህንድ ህዝብ ራሱን ለማዳን በቤተሰቦቹና በወዳጆቹ እንዲሁም በራሱ ላይ ብቻ ተስፋውን እንዲጥል መልእክት እስተላልፈዋል፡
አሁን ላይ በኒው ደልሂና በበሙምባይ አካባቢ በሽታው የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ ቢሆንም በአጠቃላይ ደካማ የጤና ፖሊሲ ባላት ህንድ የቫይረሱ ስርጭት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ መምጣቱ ተስተውሏ፡፡አልጀዚራ እንደዘገበው የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሚዲ መንግስት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚችለውን ሁሉ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግሯል፡፡
መሬት ላይ የሚታየው እውነታ ግን የህንድ ህዝብ በቫይረሱ ሳቢያ ነገውን መተንበይ የማይችልበት ስጋት ውስጥ መግባቱን ነው፡