loading
በሻርም አል-ሼክ ለህዝብ ይፋ የተደረገው የሞሀመድ ሳላህ ቅርፅ አነጋጋሪ ሁኗል

በሻርም አል-ሼክ ለህዝብ ይፋ የተደረገው የሞሀመድ ሳላህ ቅርፅ አነጋጋሪ ሁኗል

አርትስ ስፖርት 27/02/2011
የሊቨርፑል እና የግብጽ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች በሆነው በሞሃመድ ሳላህ ቅርጽ የተሰራው ሃውልት የበርካቶች መቀለጃ እና መሳለቂያ እየሆነ ነው፡፡
ይህን ሃውልት የቀረፀቸወው ቀራጺዋ ማያ አብደላህ ለግብጽ መገናኛ ብዙሃን ይህን ልዩ የሆነ የጥበብ ሥራ የሰራሁት ሞሐመድ ሳላህ ለግብጻውያን ወጣቶች የስኬታማነት ምልክት አድርጌ ስለምወስደው ነው ብትልም መሳለቂያ መሆኑን ቀጥሏል፡፡
ተጫዋቹ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የሚገልጽበትን አካላዊ ሁኔታ በሚገልፅ መንገድ ተቀርጿል የተባለው ይህ ሃውልት ቅርጹ ሞሃመድ ሳላህን ስለመምሰሉ ግን ብዙዎች እየተጠራጠሩ ነው። የተጫዋቹን ክብርም ያወረደ ነው እየተባለ በባለሙያዎችና ስፖርት ወዳዱ ማህበረሰብ እየተተቸ ይገኛል፡፡
በርካቶች በፌስቡክ እና በቲውተር ገፃቸው ከዚህ ቀደም በክርስቲያኖ ሮናልዶ አምሳል ተሰራ ከተባለው ሃውልት ጋር ሰዎች በማነፃፀር እየተሳለቁበት ነው ተብሏል፡፡
ቅርፁ ሞ ሳላህን ከመምሰል ይልቅ ድምፃዊ ሊዮ ሳየር ወይንም Home Alone ከተሰኘው ፊልም ውስጥ ሌባውን ማርቭን እንደሚመስል እየተነገረ ይገኛል፡፡
ይህ የጥበብ ሥራ በግብጽ ሻርም አል-ሼክ ስታዲየም ባሳለፍነው እሁድ የግብፁን ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች በተገኙበት የአለም ወጣቶች ፎረም ነበር ለህዝብ ይፋ የተደረገው፡
ቢቢሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *