loading
በባህሬን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ የቦንድ ግዥ ተፈጸመ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014  በባህሬን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ የቦንድ ግዥ ተፈጸመ:: የኢትዮጵያ አዲስ ዓመትም ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት አምባሳደር ጀማል በከር፣ ዲፐሎማቶችና ሰራተኞች፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ በባህሬን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጰያዊያን በተገኙበት ተከብሯል።

አምባሳደር ጀማል በከር ለኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳቸሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የብልጽግናና ስኬት እንዲሆንም ተመኝተዋል። በባህሬን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በባህሬን የዜጎቻችን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ እያደረጉ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አድንቀው ይህንኑ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በህገወጥ የሰዎችና የገንዘብ ዝውውር የሚሳተፉ ሰዎችን ሁሉም ተባብሮ ለህግ ማቅረብ እንደሚገባ አሳስበዋል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር ውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ ‘የኛ የኢትዮጵያዊያን የሉዓላዊነት መገለጫችን የሆነውን የታላቁ ህዳሴ ግድባችን በይቻላል መንፈስ እንደጀመርን እንጨርሰዋለን’ በሚል መሪ ቃል ከ10,ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ የቦንድ ግዥ ተፈጽሟል። የህዳሴ ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድረስ እንዲሁም መንግስት የያዛቸውን ዘርፋ ብዙ ግቦች እንዲሳካ የድርሻቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ኤምባሲው ገልጿል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *