loading
በቱኒዚያ በልዑሉ ላይ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

አርትስ 18/03/2011

የሳውዲው ልኡል አልጋ ወራሽ ሞሀመድ ቢን ሳልማን የዓረብ ሀገራትንና የሰሜን አፍሪካ ጉብኝታቸውን ቀጥለው ካይሮ ገብተዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው አልጋ ወራሹ የካይሮ ቆይታቸው ሲጠናቀቅ ቀጣይዋ መዳረሻቸው ቱኒዚያ ናት፡፡

ይሁንና በካይሮ የተደረገላቸው አይነት መልካም አቀባበል በቱኒዚያ እንደማይጠብቃቸው እየተነገረ ነው፡፡

በርካታ የቱኒዝ ነዋሪዎች  የልዑሉን ወደ ሀገራቸው መምጣት በመቃወም ጎዳና ወጥተው እንዳይመጡባቸው መንግስታቸውን ጠይቀዋል፡፡

የተቃውሟቸው ምክንያት ደግሞ በሳውዲ አረቢያዊው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጂ ግድያ የልዑሉ እጅ አለበት የሚል ነው፡፡

የተቃውሞ ጥሪውን ያስተባበሩት የቱኒዚያ የጋዜጠኞች ማህበር፣ 13 የሚሆኑ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም የሲቪክ ማህበራት በጋራ በመሆን ነው፡፡

የተቃውሞ ሰልፈኞቹ እዚህ አደባባይ የተሰባሰብነው ማንኛውም ወንጀል የሰራ መሪ ወደ ሀገራችን መምጣት እንደሌለበት ለማሳየት ነው ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *