loading
በአንድ ሳምንት ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 በአንድ ሳምንት ውስጥ ክብረ ወሰን የሆነ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር ተመዘገበ ከዲሴምበር 22 እስከ 28 ባለው ጊዜ በየቀኑ በአማካይ 935 ሺህ ገደማ ሰዎች በቫይረሱ ይያዙ እንደነበር አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ በዓለማቸው በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ይህም በሽታው ከተከሰተ ወዲህ ትልቁ ቁጥር ነው ተብሏል፡፡


መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከፍተኛ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር ከተመዘገቡባቸው መካከል አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና እንግሊዝ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡
ኦሊቨር ቬራን ረቡዕ እለት ሀገራቸው በ24 ሰዓታት ውስጥ 208 ሺህ የኮቪድ-19 ታማሚዎችን ማስመዝገቧን በመግለጽ አስጨናቂ ጊዜ ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡


እንግሊዝም በተመሳሳይ ቀን ከ183 ሺህ በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ የተያዙባት ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም ከተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር በ50 ሺህ ጨምሮ ታይቷል ነው የተባለው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት አሁን ላይ ዴልታ እና ኦሚክሮን የተባሉት የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች መንትያ ስጋቶች ሆነው ዓለማችንን እያስጨነቁት ነው ብሏል፡፡ የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ሲከበር የበሽታውን ስርጭት እንዳያባብሰው በመስጋት ጣሊያንን ጨምሮ አንዳንድ ሀገራት በዓሉ በአደባባይ እንዳይከበር እገዳ ጥለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *