loading
በአንድ ወር ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ ህግ እና ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች ተቀጡ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 በአንድ ወር ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ ህግ እና ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች ተቀጡ:: ባሳለፍነው መስከረም ወር ብቻ ከ10 ሺህ በላይ የትራፊክ ህግ እና ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎችን መቅጣቱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋከል፡፡ ኤጀንሲው በመስከረም ወር ብቻ የትራፊክ ህግ እና ደንብን ለማስከበር ባደረኩት የቁጥጥር 10 ሺህ 711 አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንብ ሲተላላፉ ይዣቸዋለሁ ብለሏል፡፡

በተደረገው ቁጥጥር አሽከርካሪዎቹ ፍፁም መቆም የሚከለክሉ ቦታዎች ላይ ማቆም፣ የትራፊክ መብራት መጣስ፣ ባልተፈቀደ ተቃራኒ አቅጣጫ ማሽከርከር፣ የአውቶቡስ ፌርማታዎች ላይ ማቆም፣ የመሳሰሉት የደንብ መተላለፎች መፈጸማቸው ታውቋል፡፡ እንዲሁም የተሽከርካሪን ፍሰት በሚያውክ መልኩ በሰያፍ መቆም፣ ለጊዜያዊ ማቆሚያነት የተፈቀዱ መንገዶች ላይ ደርቦ ማቆም እና አሽከርከሪዎችን ለቅጣት የዳረጓቸው የደንብ መተላለፎች መሆናቸውን
ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

ኤጀንሲው በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ፣ ፍሰቱ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ዘመናዊ የትራንስፖርት ስርዓት ለመገንባት ከማሻሻያ ስራዎች በተጨማሪ የትራፊክ ህግ እና ደንብ እንዲከበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *