በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ሊቨርፑልና ዶርትሙንድ ሲሸነፉ ባርሴሎና ነጥብ ጥሏል
በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ሊቨርፑልና ዶርትሙንድ ሲሸነፉ ባርሴሎና ነጥብ ጥሏል
አርትስ ስፖርት 28/02/2011
ትናንት ምሽት ከምድብ አንድ እስከ አራት የሚገኙ ቡድኖች የምድብ አራተኛ ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡ በምድብ አንድ አትሌቲኮ ማድሪድ ዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ላይ በሳውል ንጉኤዝ እና ግሪዝማን ግቦችታግዞ ቦርሲያ ዶርትሙንድን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ እዚሁ ምድብ በሄንሪ የሚሰለጥነው ሞናኮ በሜዳውና ደጋፊው ፊት በክለብ ብሩዥ የ4 ለ 0 አሳፋሪ ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ ምድቡን ዶርትሙንድና አትሌቲኮበእኩል ዘጠኝ ነጥቦች ይመሩታል፡፡ ምድብ ሁለት ላይ ወደ ጣሊያን የተጓዘው ባርሴሎና ያለ ሜሲ አገልግሎት ከኢንተር ሚላን ጋር አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይቷል፡፡ ማልኮም ባርሳን ቀዳሚ ያደረገችግብ ቢያስቆጥርም ኢካርዲ ኢንተርን የአቻነት ጎል ከመረብ አገናኝቷል፡፡ ባርሳ ከምድቡ አስቀድሞ በ10 ነጥቦች ወደ ጥሎ ማለፉ ተሸጋግሯል፡፡ ቶተንሀም በዌምብሌ ፒ.ኤስ.ቪ አይንዶቨንን በሀሪ ኬንሁለት ግቦች ታግዞ 2 ለ 1 ረትቷል፡፡ በሶስተኛው ምድብ ደግሞ ወደ ሰርቢያ ያቀናው ሊቨርፑል በስረቭና ዝቨዝዳ የ2 ለ 0 አስደንገጭ ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ እዚሁ ምድብ ናፖሊ እና ፒ.ኤስ.ጂ እንድ አቻበሆነ ውጤት ተለያይተዋል፤ የፈረንሳዩን ክለብ ቤርናት ሲያስቆጥር ኢንስኜ አቻ አድርጓል፡፡ በምድቡ ናፖሊና ሊቨርፑል በእኩል ስድስት ነጥቦች በመያዝ አንደኛና ሁለተኛ ሲሆኑ ፒ.ኤስ.ጂ በአምስት ነጥብሶስተኛ ነው፡፡ እዚህ ምድብ ላይ ወደ ተከታዩ ዙር የሚያልፈው ክለብ ልብ ሰቃይ ሁኗል፡፡ በአራተኛው ምድብ ደግሞ ፖርቶ በሜዳው ሎኮሞቲቭ ሞስኮን 4 ለ 1 በመርታት የምድቡን መሪነት በ10 ነጥብከፍ አድርጓል፡፡ ሻልከ 04 ደግሞ ጋላታሳራይን በ2 ለ 0 ውጤት ድል በማድረግ በ8 ነጥብ ይከተላል፡፡ ዛሬ ምሽት ከምድብ አምስት እስከ ስምንት የሚገኙ ክለቦች የምድብ አራተኛ ጨዋታቸውንያደርጋሉ፡