በአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ለአንድ አመት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው ::
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 በአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ለአንድ አመት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው ::በአዲስ አበባ የሚገኙ 2 ሺህ አካል ጉዳተኞች ለአንድ አመት ያህል ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ሊያገኙ መሆኑን የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አካል ጉዳተኞች የእውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።
የትራንስፖርት አገልግሎቱን የሚያገኙት በብሎክ አደረጃጀት የተመረጡ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች መሆናቸውም ታውቋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ጃንጥራር አባይ፤ አካል ጉዳተኞችን ማገዝ፣ መርዳትና የተለያዩ ህጎችና ፖሊሲዎችን ቀርፆ መስራት የመንግስት ድርሻ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።በመሆኑም በመንግስት በኩል እየተሰሩ ያሉ ጅምር እንቅስቃሴዎችን ለማስፋት የተለያዩ አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።