loading
በአፍጋኒስታን ጉዳይ አሁንም አቋሜ የጸና ነው -ጆ ባይደን

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013  የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአፍጋኒስታን ወታደሮቼን በማውጣት ውሳኔዬ የምጸጸትበት አይደልም ሲሉ ተናገሩ፡፡ አንድም የአሜሪካ ወታደር በአፍጋኒሰታን ምድር ሊሞት አይገባም ያሉት ባይደን በአወጣጥ ላይ ክፍተቶች እንደነበሩ አልሸሸጉም፡፡ ጆ ባይደን ማስተባበያ በሰጡበት በዚህ ንግግራቸው እንዳብራሩት፣ የአፍጋኒሰታን ጦር ታሊባንን ለመዋጋት ፍላጎት እንዳልነበረው፤ የአፍጋኒሰታን መንግሥትም ወዲያውኑ ተስፋ እንደቆረጠ ከገለጹ በኋላ ፤ታሊባን
ካቡልን ይቆጣጠራል ብለን ከገመትንበት ጊዜ ቀድሞ መምጣቱ ነገሮችን እንዳመሰቃቀለ አመላክተዋል፡፡

በሳምንቱ መጨረሻ ስለሆነው ነገር ለመጀመርያ ጊዜ አስተያየት የሰጡት ባይደን፤ ባለፈው ሳምንት በአፍጋኒስታን የሆነው ነገር አንድ ያረጋገጠልን ጉዳይ ቢኖር ከዚያች አገር ለመውጣት መወሰናችን ትክክል እንደነበረ ነው ብለዋል፡፡ አንድም የአሜሪካ ወታደር በአፍጋኒስታን መዋጋት የለበትም፣ መሞትም የለበትም፣ የአፍጋኒስታን ወታደሮች ለማይዋጉለትና ለማይሞቱለት ጦርነት ለምን ብሎ አሜሪካዊ ወታደር ተዋግቶ ይሞታል ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ከ20 ዓመት በፊት የአሜሪካ ወታደሮች አፍጋኒስታንን እንዲወሩ ያደረጉት ጆርጅ ቡሽ በበኩላቸው በአፍጋኒስታን እየሆነ ያለውን ነገር በታላቅ ሐዘን ነው እየታዘብኩ ያለሁት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጆ ባይደን የአሜሪካ በአፍጋኒስታን ተልዕኮ አገር ግንባታ አልነበረም ያሉ ሲሆን፤ በ2009 ባራክ ኦባማ ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ አፍጋኒስታን ሲልኩ ተቃውመዋቸው እንደነበረ እና ትራምፕ ከአፍጋኒስታን ለመውጣት በግንቦት ወር እቅድ ይዘው የነበረ መሆኑን፤ እሳቸው ደግሞ የ20 ዓመት የአፍጋኒስታን
ቆይታን እንዲቋጭ ለመወሰን 4ኛው ፕሬዚዳንት እንደሆኑ መናገራቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *