loading
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተጀመረውን ግንኙነት ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ፍኖተ ካርታ ተዘጋጀ፡፡

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተጀመረውን ግንኙነት ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ፍኖተ ካርታ ተዘጋጀ
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተጀመረውን ግንኙነት በተቋማዊ አሰራር ለመደገፍ የሚያስችል የትብብር ፍኖተ ካርታ ተለይቶ መዘጋጀቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል።

የሚኒስቴሩ የ2011 ዓ/ም የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  በገመገመበት ወቅት ፍኖተ ካርታው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰብሳቢነት በገንዘብና ኢኮኖሚ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ትብብር ተለይቶ መዘጋጀቱ ተነግሯል።

በፍኖተ ካርታው መሰረትም በሁለቱ ሃገራት መካከል የሚኖረው የድንበር ንግድ፣የወደብ አጠቃቀም ፣ የጉምሩክ ፣የኢምግሬሽንና የትራንስፖርት ትብብሮች የሚመሩበት ህጋዊ ማዕቀፍ ለመፍጠር ረቂቅ የስምምነት ህጎች ዝግጅት ተጠናቆ ለኤርትራ ወገኖች ደርሶ ውይይት ተደርጎበታል።

በቀጣይ በሁለቱ ወገኖች አጠቃላይ የሁለትዮሽ ትብብር እና የጋራ ኮሚሽን መቋቋሚያ ስምምነት እንደሚፈረምም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *