በኦሮሚያ ክልል ደረጃ 42 የነበሩ መስሪያ ቤቶችና አደረጃጀቶች ወደ 38 ዝቅ ተደርጉ፡፡
አርትስ 28/01/2011 ዓ.ም
ይህም ዉሳኔ የተላለፈዉ ጨፌ ኦሮሚያ የስራ አስፈፃሚ አካላትን መልሶ ለማደራጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ዛሬ በማጽደቁ ነዉ፡፡
በዚህ መሰረት በአዋጅ 199/2008 መሰረት በክልል ደረጃ 42 የነበሩ መስሪያ ቤቶችና አደረጃጀቶች አዲስ በጸደቀው አዋጅ መሰረት 38 ተደርገዋል፡፡
ጨፌው አዳዲስ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ አደረጃጀቶችንም አዋቅሯል፡፡