loading
በካሜሮን የታገቱ ተማሪዎችን ፍለጋ ቀጥሏል

በካሜሮን የታገቱ ተማሪዎችን ፍለጋ ቀጥሏል

አርትስ 28/02/2011

 

የካሜሮን ባለ ስልጣናት ባለፈው ሰኞ በታጠቁ ሀይሎች ታግተው የተወሰዱ 79 ተማሪዎች እና 3 የትምህርት ቤቱ የስራ ባልደረቦችን ፈልጎ በህይወት የማገኘቱ ስራ በአስቸኳይ እንዲከናወን ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

የሀገሪቱ ሰሜን ምእራብ አስተዳዳሪ ዲበን ቻፎ እንዳሉት ከተማሪወቹ በተጨማሪ የትምህርረት ቤቱ ሀላፊ፣ ሾፌርና መምህር በነዚህ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የካሜሮን ወታደራዊ ቃል አቀባይ በሀገሪቱ የእንገንጠል ጥያቄ የሚያነሱ ሀይሎች ናቸው ድርጊቱን የፈፀሙት በማለት ሀላፊነቱን ይወስዳሉ ብለዋል፡፡

የሀይማኖት አባቶች በበኩላቸው ድርጊቱን አውግዘው ህጻናቱና የትምህርት ቤቱ ሰራተኞች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተማሪወቹ የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ስም እንዲናገሩ በአጋቾቻቸው ሲጠየቁ  በማህበራዊ ድረ ገፅ በተለቀቀ የቪዲዮ ምስል ታይተዋል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *