loading
በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ጅማ አባ ጅፋር ድል ሲቀናው፤ ዛሬ መከላከያ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይጫወታል

አርትስ ስፖርት 19/03/2011

ለ23ኛ ጊዜ በሚካሄደው የቶታል ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች እየተካሄዱ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያን የወከለው ጅማ አባ ጅፋር ጅቡቲ ላይ ጅቡቲ ቴሌኮም ክለብ ጋር ተጫውቶ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ድል በማድረግ መልካም ጉዞውን ጀምሯል፡፡ ለጅማው ቡድን ማሊያዊው አጥቂማመዱ ሲዲቤ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፣ አስቻለው ግርማ ቀሪዋን ግብ ከመረብ አገናኝቷል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ የመልስ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ወደቀጣዩ ዙር የሚያልፈው ክለብ አል አህሊን የሚገጥም ይሆናል፡፡

ለ16ኛ ጊዜ በሚካሄደው የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ፤ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ተካፋይ የሚሆነው የመከላከያ እግር ኳስ ቡድን ደግሞ ዛሬ ከናይጀሪያው ሬንጀርስ/ኢኑጉ ኢንተርናሽናል ጋርከቀኑ 10፡00 ሲል ኢኑጉ ላይ በንናምዲ አዚኪዌ ስታዲየም ይጫወታል፡፡

መከላከያ በኮንፌዴሬሽን ዘንድሮ ሲሳተፍ በአራት ዓመት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ቢሆንም ቅድመ ማጣሪያውን ግን መሻገር እንኳ አልቻለም፡፡

ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል በናይጀሪያ ፕሪምየር ሊግ ከሊጉ ወርዶ የማያውቅ ብቸኛው ክለብ ሲሆን በአህጉር አቀፍ ውድድሮች ከመከላከያ ከፍ ያለ ስም አለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *