loading
በኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡

በኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡

ይህ የተባለዉ የገቢዎች ሚኒስቴር  ኮንትሮባንድን ለመከላከል ከፍትህ አካላት ጋር በአዳማ  የዉይይት መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነዉ፡፡

በመድረኩ ኮንትሮባንድ በየቦታው ኬላዎችን በማደራጀት ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ኮንትሮባንድን በመያዝ፣ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የሚያውሉ፣ ምርምራ የሚያደርጉ እና ውሳኔ የሚሰጡ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባልም ብለዋል፡፡

ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር ጠንካራ የህግ ማቀፍ ሊኖር እንደሚገባም ተነግሯል፡፡ የህግ ማቀፎቹ የጉምሩክ ኮሚሽን እርምጃ መወሰድ የሚያስችለው ስልጣን የሚያጎናፅፉት መሆን አለባቸውም ተብሏል፡፡

ኮንትሮባንድን በሚያሳልፉ አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበትና የተሻለ የሰሩ እውቅና የሚሰጥበት አሰራር መዘርጋት ያስፈልጋል

ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች በስፋት ሊሰሩ ይገባል የተባለ ሲሆን፤በአስፈፃሚ አካላት መካከል የሚታዩ የቅንጅት ችግሮች መፈታት አለባቸውም ተብሏል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ፤ኮንትሮባንድ የሚያስከትለውን ችግር ለመከላከል የፍትህ አካላት የተባበረ ስራ የሚያስፈልገው እንደሆነ ውይይቱን በከፈቱበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

በኮንትሮባንድ ንግድ የሚሳተፉ አካላት ላይ በቀጣይ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ ከፍትህ አካላት ጋር አንድ አቋም መያዝ ያስፈልጋል፡፡ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት መፍትሄው ላይ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የኦሮሚያ ክ/መ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ደሳ ቡልቻ በበኩላቸው የፍትህ አካላት ህጋዊ አሰራርን ተከትሎ በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ በጋራ ከሰራን ችግሩን በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍታት ይቻላል ነው ያሉት፡፡
በአዳማ ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ዳኞች፣ አቃቤያን ህጎች እና በፍትህ ስርዓት ውስጥ ድርሻ ያላቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *