loading
በኮንጎ ቤኒ ግዛት ምርጫ በመራዘሙ አሁንም ተቃውሞው ቀጥሏል

አርትስ 18/04/2011

በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ከሶስት ጊዜ በላይ የተራዘመው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በመ ጭው እሁድ እንዲካሄድ ቁርጥ ቀን ቢያዝለትም በተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች በዚህ ቀን ምርጫ እንደማይካሄድ ተረጋግጧል፡፡

ይህን ተከትሎም የአካባው ነዋሪዎች ቁጣቸው ገንፍሏል ነው የተባለው፡፡ በነዚህ አካበባቢዎች ምርጫ እንዳይካሄድ ውሳኔውን ያሳለፈውን የምርጫ ኮሚሽንም አጥብቀው አውግዘዋል፡፡

ፖሊስም ለተቃውሞ ጎዳና የወጡ ሰዎችን ለመበተን ጥይት ወደ ሰማይ ሲተኩስ እንደነበር ሮይተርስ በዘገባው አስነብቧል፡፡

በቤኒ፣ ቡቴምቦና ዩምቢ አካባቢዎች ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ሰላማዊ እንቅስቃሴ ባለመኖሩ ነው ኮሚሽኑ ምርጫው በዘኒህ ከተሞች እንዳይካሄድ የወሰነው፡፡

ሰልፈኞቹ ወደ ምርጫ ኮሚሽኑና የከተማዋ ከንቲባ ቢሮዎች መፈክሮችን ይዘው የተቃውሞ ድምፃቸውን እያሰሙ ለመግባት በመሞከራቸው ከፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡

አሁን ምርጫው እንዳይካሄድ በተከለከለባቸው አካባዎች ሳይጨምር በሚካሄደው ምርጫ በሚሰጠው ድምፅ ውጤቱ በፈረንጆቹ ጥር 15 ይፋ እንዲሆን መርሀ ግብር ተይዞለታል፡፡

አሸናፊው ፕሬዝዳንት ደግሞ ውጤቱ በይፋ ለመራጩ ህዝብ ከተገለፀ ከሶስት ቀናት በኋላ ቃለ መሀላ ፈጽሞ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ በወጣትነት እድሜያቸው ገብተው የጎለመሱበትን ቤተ መንግስት ይረከባል ተብሏል፡፡

የሀገሪቱ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫው ከመጭው እሁድ በኋላ የሚራዘም ከሆነ ደጋፊዎቻቸው የነሱን ትእዛዝ ሳይጠብቁ መብታቸውን እዲያስከብሩ አስጠንቅቀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *