loading
በደሴና ድሬዳዋ አካባቢዎች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ሺሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በደሴና ድሬዳዋ አካባቢዎች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ሺሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ የያዝኳቸዉ እቃዎች በድምሩ ከ1,073,021 ብር በላይ የሚገመቱ  ናቸዉ ብሏል፡፡

ከነዚህ ዉስጥ ግምታዊ ዋጋው 572,481 ብር የሚደርስ ኮንትሮባድ ሲጋራና ምስር ወደ ድሬዳዋ ከተማ ለማስገባት ሲሞከር የተያዘ ሲሆን፤ ኮንትሮባንዲስቶቹ ተኩስ በመክፈት የኮንትሮባድ ዕቃዎቹን ለማሳለፍ ሙከራ አድርገዉም  ነበር ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ መስመር 350 ሺህ ብር የሚጠጋ እርጥብ ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር በጉምሩክ ሰራተኞችና በመከላከያ ሰራዊት የጋራ ጥረት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ግምታዊ ዋጋው 316,200 የሆነ የምግብ ዘይት በኤፍኤስ አር ተሽከርካሪ በአማራ ክልል በጉባ ላፍቶ ወረዳ ሀራ ተብሎ የሚጠራ ቦታ በክልሉ ፖሊስ አባላት የተያዘዉም በዚህ ሳምንት ነዉ፡፡

ሸዋሮቢት አካባቢ በሀሰተኛ ደረሰኝ 34,340 ብር የሚገመት ሽቶ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ እና  ደሴ ከተማ ውስጥም 719 ስቴካ ሺሻ መያዛቸዉንም ሰምተናል፡፡

ምንጭ ፤-ገቢዎች ሚኒስቴር

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *