በጋና ቢጫ ጄሪካኖች ለመንገድ ንጣፍነት እየዋሉ ነው
አርትስ 13/02/2011
በጋና ዋና ከተማዋ አክራ ለአቧራማ መንገዶች የጄሪካን ቁርጥራጮች እንደ ኮብልስቶን ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው፡፡ የከተማዋ ወጣቶች አቧራማ የሆኑ የሰፈሩን መንገዶች ከቢጫ ጀሪካን በተቆራረጡጌጦች እያስዋቡ ነው፡፡
አገልግሎት ላይ የሚውሉት ቢጫ ጄሪካኖች ኩፎር ጋሎን ተብለው ይጠራሉ። ጆን ኩፎር የቀድሞ የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ስም ሲሆን፤ በእሳቸው የአመራር ዘመን ከባድ የውሃ እጥረት አጋጥሞ፤ ሰዎችእነዚህን ጄሪካኖች ይዘው ለውሃ ፍለጋ ይወጡ ስለነበር ነው ጄሪካኖቹ ይህን ስያሜ ያገኙት፡፡
ክሎቴ የተባለው ወጣት ይህንን አጋጣሚ ወደ ሥራ ቀይሮ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ወደ ቆሻሻ መጣያዎች በመሄድ ጄሪካኖቹን ይሰበስባሉ ከዚያም በቅርፅ ይዘጋጁ እና እንደ ኮብልስቶን በአቧራማ መንገዶች ላይ ይነጠፋሉ፡፡
ቢቢሲ