loading
በ33 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባዉ የዱከም ብረታብረት ፋብሪካ ተመረቀ

በ33 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባዉ የዱከም ብረታብረት ፋብሪካ ተመረቀ

አርትስ 07/02/2011

በኮሪያ ባለሃብቶች የተገነባዉና 33 ሚሊዮን ዶላር የወጣበት ኢኮስ ብረታብረት ፋብሪካ ተመርቋል፡፡

በምርቃ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ኢትዮጵያ ከኮሪያ ጋር በባህልና በፖለቲካ የረጅም አመታት የጠበቀ ትስስር ያላት መሆኑን ጠቅሰዉ በኢንቨስትመንት ዘርፍም የኮሪያ ባለሃብቶች በሃገሪቱ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደሩ ሁን ሚን ሊም በበኩላቸዉ ሃገራቸዉ ከኢትጵያ ጋር በሁሉም መስክ ያላትን ግንኙነት አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ይህ ፋብሪካ ማሳያ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አምባሳደሩ አክለዉም ኮሪያዉያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በሌሎች ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ ወይዘሮ ጠይባ ሃሰን ፋብሪካዉ ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥርና ለህብረተሰቡ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለዉ መሆኑን ጠቅሰዉ ክልሉ ለኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚያደርገዉን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *