loading
ቡናችን በዓለም ገበያ የሚፈለገዉን ያህል አልተዋወቀም ተባለ

ይህ የተባለዉ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንና ከቡና ላኪዎች ማህበር ጋር በጋራ ባዘጋጁት ቡናን በአለም ማስተዋወቅ ላይ ባተኮረ የዉይይት መድረክ ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ የቡናና ሻይ ባለስልጣን የገበያ ልማት ቁጥጥርና የግብይት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር በሀገራችን ከ25 ሚሊየን በላይ ህዝብ ኑሮዉ በቡና ምርት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የምናመርተዉ ቡና ግን ጥራቱን የጠበቀ ባለመሆኑ አምራቹን መጥቀም አልተቻለም ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ተፈራ በአመት 400 ሺ ቡና ብናጓጉዝም ዘላቂነቱን የጠበቀ ባለመሆኑ ምክንያት ከኢትዮጵያ ቡና ይልቅ የሌሎች ሀገራት ቡና ተመራጭ ሲሆን ይስተዋላል ብለዋል፡፡
ቡናችንን በተገቢዉ ማስተዋወቅ አለመቻሉ ዋነኛ ችግር ስለሆነ ይህን ችግር ለመቅረፍ ቡና ምርት በብዛት በሚደርስበት በሕዳር ወር አለም አቀፍ የቡና ቀንን ሀገራችን ኢትዮጵያ ታከብራለች ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *