ባህር ውስጥ የተከሰከሰው የኢንዶኔዠያ አውሮፕላን ጥቁር ሳጥን ተገኘ
ባህር ውስጥ የተከሰከሰው የኢንዶኔዠያ አውሮፕላን ጥቁር ሳጥን ተገኘ
አርትስ 22/02/2011
ከሶስት ቀናት በፊት በባህር ውስጥ የመከስከስ አደጋ የደረሰበት የኢንዶኔዢያ አውሮፕላን ጥቁር ሳጥን ዛሬ በባህሩ ዳርቻ አካባቢ መገኘቱ ተነግሯል።
የአውሮፕላኑን ስብርባሪ ለማግኘት ፍለጋ የተሰማሩ ጠላቂዎች የአውሮፕላኑን የበረራ መረጃ የያዘውን ጥቁር ሳጥን ማግኘታቸው የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ በእጅጉ ይረዳል ተብሏል።
ሜትሮ የተባለው የኢንዶኔዢያ ቲሌቪዠን ጣቢያ እንደዘገበው 189 ሰዎች አሳፍሮ ከኢንዶኔዢያ ዋና ከተማ ጃካርታ የተነሳው አውሮፕላን ከደቂቃዎች በኋላ ድንገት ጃካርታ ባህር ውስጥ መከስከሱ ይታወሳል።
ከዓለም እጅግ አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋዎች ሁለተኛው ነው በተባለው በዚሁ አደጋ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች በሙሉ አልቀዋል።
ቦይንግ ኩባንያ የኢንዶኔዢያ ባለስልጣናትን ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
ንብረትነቱ የኢንዶኔዥያ የሆነው ይኸው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ከተነሳ 13 ደቂቃ በኋላ ነው ድንገት ከዋናው ጣቢያ ጋር የነበረው ግንኙነት የተቋረጠው።
አውሮፕላኑ የሚያመራው ፓንግካል ፒናንግ ወደተባለችው የኢንዶኔዢያ ሌላዋ ከተማ ነበር።