ግብፅ በታሪኳ እንደዚህ አይነት ፈተና ገጥሟት አያውቅም አሉ የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ::
አዲስ አበባ፣ሐምሌ16፣ 2012 ግብፅ በታሪኳ እንደዚህ አይነት ፈተና ገጥሟት አያውቅም አሉ የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በቅርቡ በተመሰረተችው አዲሷ አልኣሚ ከተማ ሚንስትሮችን ሰብስበው በመንግስት አጀንዳዎች ዙሪያ ባወያዩበት ወቅት ነው፡፡ሀገራችን ከውጭም ከውስጥም እንደዚህ አይነት ፈተና ገጥሟት አያውቅም ያሉት ማድቡሊ በተለይ በሲናይ በረሃ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ብዙ ውጣ ውረዶች እንዳሉባቸው ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ማድቡሊ የሙስሊም ወንድማማቾች ዓላማ አራማጅ የነበሩትን ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲን ካስወገድን በኋላ ሽብርተኝነትን ባአግባቡ እየታገልንው ነው ብለዋል፡፡ ኢጂፕት ቱደይ እንደዘገበው ግብፅ በሲናይ በርሃ ከሽብርተኞች ጋር ባደረገችው ውጊያ በርካታ ወታደሮቿ
መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ አሁን ላይ ደግሞ ግብፅ በሊቢያ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችላት ውሳኔ በፓርላማ ማፀደቋ ከቱርክ ጋር ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብታለች፡፡ ቱርክ ዓለም አቀፍ እውቅና ላለው የሊቢያን መንግስት ወታደራዊ ድደጋፍ እያደረገች ሲሆን ግብፅ ደግሞ የጄኔራል ከሊፋ ሀፍታርን ጦር ለመደገፍ ተዘጋጅታለች ነው የተባለው፡፡