loading
ተጠባቂው የኤፍ ኤ ዋንጫ ዛሬ ምሽት ይደረጋል፡፡

ተጠባቂው የኤፍ ኤ ዋንጫ ዛሬ ምሽት ይደረጋል፡፡

 

የኤምሬትስ ኤፍ.ኤ ዋንጫ የአምስተኛ ዙር ጨዋታዎች ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ ተካሂደዋል፡፡

 

ዛሬ ምሽት 4፡30 ላይ ደግሞ የማውሪዚዮ ሳሪው ቼልሲ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ማንችስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡

 

 

በአምናው ሻምፒዮን ሰማያዊዎቹ በኩል፤ ስማቸው ያልተጠቀሱ ተጫዋቾች ጤንነት እየተፈተሸ እንደሆነ ተገልጧል፡፡

 

 

በማልሞው የኢሮፓ ሊግ ግጥሚያ በጀርባ ህመም ያልተሰለፈው ሩበን ሎፍተስ- ቺክ እና ዕረፍት የተሰጠው ማርኮስ አሎንሶ ወደ ሜዳ እንደሚመለሱ ይጠበቃል፡፡

 

 

በቀያይ ሰይጣኖቹ በኩልም፤ አጥቂዎቹ አንቶኒ ማርሽያል እና ጄሴ ሊንጋርድ በብሽሽት እና ቋንጃ ጉዳት ከምሽቱ ፍልሚያ ውጭ ሆነዋል፡፡

 

 

የኦሌ ጉናር ሶልሻዬሩ ዩናይትድ ከቻምፒዮንስ ሊግ ሽንፈት መልስ፤ የሳሪው ቡድን ደግሞ ከኢሮፓ ሊግ ድል መልስ የሚያደርጉት ጨዋታ ላይ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ድል የሚቀናው ከሆነ በተከታታይ አምስት የኤፍ ኤ ዋንጫ ግንኙነቶች ቀያይ ሰይጣኖችን በማሰናበት ቀዳሚው ቡድን ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *