ቴል አቪቭ ከዋሽንግተን ሌላ ውለታ እየጠበቀች ነው፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤናሚን ኔታናያሁ እራኤል ከሶሪያ በሀይል የወሰደችውን የጎላን ተራራን የባለቤትነት እውቅና እንድትሰጣት አሜሪካን አጥብቀው ጠይቀዋል፡፡
ከአሁን ቀደም እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ናት የሚለውን ውሳኔ ያሳለፈው የትራምፕ አስተዳደር አሁን ደግሞ ለጎላን ተራራ ሌላ እውቅና እንዲሰጠን የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ብላል ኔታናያሁ፡፡
ኔታናያሁ ይህን ያሉት የአሜሪካው የደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን ሀገራቸው እስካሁን የጎላን ተራራ ለእስራኤል ይገባታል የሚለውን እውቅና የመስጠት ሀሳብ እንደሌላት ለሮይተርስ መናገራቸውን ተከትሎ ነው ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል፡፡
እስራኤል የጎላን ተራራን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1967 በአረብ እስራኤል ጦርነት ወቅት ወደ ራሷ ግዛት በሀይል ማጠቃለሏ ይታወሳል፡፡