loading
ትግራይ ውስጥ ለሚከሰት ችግር መንግስት ተጠያቂ አይደለም አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23፣ 2013 ከዚህ በኋላ ትግራይ ለሚከሰት ችግር የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ አይሆንም ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለፁ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና መከላከያ ሰራዊት በጋራ በሰጡት መግለጫ “ከዚህ በኋላ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለሚከሰት ችግር የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ” እንደማይሆን አስታውቀዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዴኤታው ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት መግለጫ የፌዴራል መንግስት ከዚህ በኋላ በትግራይ ክልል ዙሪያ ለሚኖር ችግር ተጠያቂ የማይሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቀሌ ለቆ በመውጣቱ ነው ብለዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ተቋማትም “ከዚህ በኋላ ዕርዳታ ደረሰ አልደረሰ ብለው የፌዴራል መንግስትን ሊጠይቁ” እንደማይገባ የገለጹት አምባሳደር ሬድዋን፤ የትግራይ ክልልን በተመለከተ ሙሉ ኃላፊነቱን አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ህወሃት እንደሚወሰድ ገልጸዋል፡፡ አምባሳደር ሬድዋን በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት ኢትዮጵያን ለከፍተኛ ኪሳራ እንደዳረጋት ገልጸው በልማት ሂደቱ ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረና በትግራይ ክልል በተደረገ ዘመቻ ከ 100 ቢሊየን ብር
በላይ መውጣቱንም አብራረርተዋል፡፡

ህወሃት የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ እንደጣለ ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው ሱዳን የኢትዮጵያን ሉኣላዊ ድንበር ጥሳ እንድትገባ አጋልጦ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡
መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ያወጀውና ወታደሮችን ከመቀሌ ያስወጣው በመንግስት ፖለቲካዊ ውሳኔ መሆኑም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡ የተኩስ አቁም ውሳኔውና ወታደሮችን ከመቀሌ የማወጣት ስራ የተሰራው ሀገርን ለተጨማሪ የሀብት ብክነት ላለመዳረግ መሆኑም ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ጦር አስፈላጊ ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ወደ ትግራይ የመመለስ ሙሉ አቅም እንዳለውም ሚኒስትር ደኤታው አብራርተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *