loading
አልማ ማህበር የህወሓት ቡድን በፈጠረ ቀውስ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የዕለት ደራሽ ድጋፍ አቀረበ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 የአማራ ልማት ማህበር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አራጋው ታደሰ እንደገለፁት በዋግ ህምራና ሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የቆቦ፣ ራያ አላማጣና ግዳን ወረዳ ነዋሪዎች በአሸባሪው ትህነግ ምክንያት ከሰላማዊ ኑሯቸው ተፈናቅለው ደሴና ወልድያ ከተማ ለሚገኙ የዕለት ደራሽ ድጋፍ አቅርበዋል። ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን እንደ አስፈላጊነቱ መፈፀም በሚያስችለው ስትራቴጅያዊ የለውጥ ዕቅድ መሰረት ቡድኑ በፈጠረው ቀውስ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች አንድ ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት 327 ኩንታል የፉርኖ ዱቄት ቦታው ድረስ በማጓጓዝ ለተፈናቀሉ ወገኞች እንዲውል ድጋፍ መደረጉን አቶ አራጋው አስረድተዋል፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አለሙ ይመር በርክክብ ስነ- ስርዓቱ ወቅት እንደገለፁት አማራ ልማት ማህበር እያከናወነ ከሚገኘው ዘላቂ ማህበራዊ ልማት ጎን ለጎን በአሸባሪው ትህነግ የተፈናቀሉ የተወሰኑ ወረዳ ነዋሪዎችን ለማቋቋም ያበረከተው የዕለት ደራሽ
ድጋፍ ሁነኛ የክልሉ ህዝብ አጋርነቱን አስመስክሯል ብለዋል፡፡

ቡድኑ በአማራ ክልል ህዝብም ሆነ በሀገር ህልውና ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ቀውስ የልማት ማህበሩ ሰራተኞች ማውገዘቸውን የገለፁት ምክትል ስራ አስፈፃሚው ፤ባለፈው ወር ጀምሮ የማህበሩ ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸው አሸባሪውን ቡድን ተግባርና አስተሳስብ ለማምከን በሚደረገው ሀገራዊ
ርብርብ ድጋፍ እንዲውል መወሰናቸውን አውስተዋል፡፡

ትህነግ በፈጠረው ቀውስ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋምም ሆነ የአሸባሪውን ቡድን ተግባርና አሰተሳሰብ ለማፅዳት የሚደረገውን የተቀናጀ የህዝብና የመንግስት ጥረት አማራ ልማት ማህበር አባላቱንና ደጋፊዎቹን በማስተባበር ድጋፉን አጠናቅሮ እንደሚቀጥል ከማህበሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *