loading
አዲሱ የኮቪድ -19 ዝርያ ደቡብ አፍሪካን እያመሳት ነዉ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21፣ 2013 ዴልታ የተሰኘው አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ደቡብ አፍሪካን ክፉኛ እየጎዳት ነዉ ተባለ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መጀመሪያ በህንድ የተገኘ ሲሆን፤ በደቡብ አፍሪካም የዚሁ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ አሳሳቢነት ከፍ እያለ በመምጣቱ አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል ተገዳለች፡፡ ሀገሪቱንም በጥር ወር ወደነበረችበት አሳሳቢ ሁኔታ እየመለሳት የሚገኘው ይህ ቫይረስ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ከ 18 ሺህ በላይ አዲስ ኬዞችን አስመዝግባለች ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ለሀይማኖታዊም ሆነ ፖለቲካዊ ተግባር መሰባሰብን የከለከለቸው ደቡብ አፍሪካ ለሚቀጥሉትም ሁለት ሳምንታት እንደሚቀጥል አሳውቃለች፡፡ በተጨማሪ የሀገሪቱ መንግስት የሰዓት እላፊን በማራዘም ለሚቀጥለው ሳምንታት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ እና ሁሉም በቤት ውስጥ በመሆን የቫይረሱን መተላለፍ መቀነስ እንደሚኖርበት አሳስቧል፡፡ አሁን እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች እየተዛመተ ያለውን ቫይረስ ፍጥነት ለመግታት በቂ እንዳልሆኑ እና ከዚ ቀደም ከነበረው የቫይረሱ ሁኔታ በላይ የዚህኛው አሳሳቢ እና የከፋ ሊሆን እንደሚችል ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አያይዘው ሀገራቸው እየተጋፈጠች ካለቸው ችግር አንፃር እና ካሏት 59 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ 2. ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ ብቻ ክትባት ማግኘት መቻሉ ሀገሪቱ ይባስ በውጥረት ውስጥ እንድትቆይ ያደርጋታል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ራማፎሳ አዲስ ወደ ሀገሪቱ እየገቡ ያሉ ክትባቶች የሀገሪቱን የክትባቱ ፕሮግራም እንዲፋጠን እና የክተባቱን ቁጥር ለመጨመር እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *