ኢራን በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ወታራዊ ልምምዶችን ማድረጓ ተሰማ፡፡
አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013 ኢራን በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ወታራዊ ልምምዶችን ማድረጓ ተሰማ፡፡ የአሜሪካ ቢ 52 ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች በመካከለኛው ምስራቅ መብረራቸውን ተከትሎ ቴህራን በሀገሪቱ ደቡባዊ ጠረፍ አካባቢ ከባድ ልምምዶችን አድርጋለች ነው የተባለው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ባለፈው ጃኑዋሪ 3 በጄኔራል ቃሲም ሰይማኒ ላይ ግድያ ከተፈፀመ ወዲህ የአሜሪካ ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች በአካባው ሲበሩ የመጀመሪያቸው ነው፡፡
ኢራን በሁለት ሳምንታት ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ ባካሄደችው የጦር ልምምድ በርካታ እግረኛ ወታደሮችና ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች እንዲሁም ታንኮች ተካፍለውበታል፡፡ የሀገሪቱ ጦር ሃይል በሰጠው መግለጫ ወታደራዊ ልምምዱ የውጊያ አቀማችን ያለበትን ረረጃ ለማወቅና ለትንኮሳ ለተዘጋጁ ጠላቶቻችን መልእክት ለማስተላለፍ ነው ብሏል፡፡
የኢራን ጦር ሃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ሞሃመድ ሁሴን ዳድራስ በድሮኖችና በሚሳኤል የታገዘው የምደር ሃይል ልምምድ ከፍተኛ የአፈፃፀም ብቃት ማሳየቱን ተገንዝበናል ነው ያሉት፡፡ በቀጠናው የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየተጠናከረ መምጣቱን ተከትሎ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ሃይል ከፍተኛ ዝግጅትና ልምምዶችን እያደረገ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ ጃቫድ ዛሪፍ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ አሜሪካ ኢራንን
ለማጥቃት የምታባክነውን ረብጣ ዶላር የግብር ከፋይ ዜጎቿን ጤና ለመበቅ ብታውለው ይሻላት ነበር በማለት ዋሽንግተንን አጥብቀው ተችተዋል፡፡