loading
ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት መጠናከር የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች መሆኑን የጸጥታዉ ምክር ቤት ገለፀ

አርትስ 04/03/2011

 

ኢትዮጵያ ላለፉት ከ70 ዓመታት  ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የነበራትን ሚና አሁንም  ለድርጅቱ መጠናከር  በሙሉ ልብለመወጣት ዝግጁ መሆኗ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ተነግሯል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ ለጽ/ቤቱ ባደረጉት ንግግር፣ የሰላም እናደህንነት ችግር የወቅቱ ፈታኝ ዓለም አቀፋዊ ስጋት መሆኑን በመጠቆም ለዚህ ችግር የጋራ ምላሽ ለመስጠት በጋራ ከሚደረግ እንቅስቃሴየተሻለ አማራጭ የለም ብለዋል፡፡

አምባሳደሩ፣ ዓለም የተጋረጠበትን ሰብዓዊ ስጋቶችን በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንዴት መቅረፍ እና ውጤታማ ማድረግ እንደሚቻልመነጋገር ይገባል ብለዋል፡፡

የተመድ የተቀናጀ የደህንነት ስርዓት የጦርነትን አደጋ፣ በርካታ የእርስ በርስ ግጭቶች፣ የአሸባሪነት እና የአክራሪነት ስጋቶች እንዲሁምድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች የዓለም ሰላም የማጣት ስጋትን እንዲጨምር ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

ድህነት፣ የበሽታ መስፋፋት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች  ለማስወገድ የተባበሩትመንግስታት ድርጅት ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚፈለግበት ወቅት በመሆኑ በትኩረት ይሰራለ ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *