ኢትዮጵያ በመጪው አመት መጀመሪያ ሳተላይት ወደ ሕዋ አመጥቃለሁ አለች፡፡
ኢትዮጵያ በመጪው አመት መጀመሪያ ሳተላይት ወደ ሕዋ አመጥቃለሁ አለች፡፡
የኢኖቪሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እነዳሰታወቀው ለአገራችን የመጀመሪያው የሆነው የሳተላይት ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል
በ2012 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹ ወራት ወደ ሕዋ ይመጥቃል የተባለው ሳተላይት ለመሬት ምልከታ ስራ ላይ ይውላል ያሉት የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ናቸው፡፡
ይኸው ሳተላይትም ለግብርና፣ ለውሃ፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለማዕድን ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ ክትትል አገልግሎት ላይ ይውላል ፡፡
በመጪው ጊዜ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ለምትገነባው ተጨማሪ የሳተላይት ግንባታ የሚሆን ፋብሪካም ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትሩ የመስሪያ ቤታቸውን የ9 ወር የስራ ክንውን ሪፖርት ለሕዝብ ተወካች ምክር ቤት ሲያቀርቡ ተናግረዋል፡፡
ለሳተላይት ፋብሪካ ግንባታ ከሚደረገው ዝግጅት በተጨማሪ የመገጣጠሚያና ፍተሻ ማዕከል ለመገንባትም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተሰምቷል፡፡
ምንጭ ፤-ሸገር