loading
ኢትዮጵያ በ2010 በጀት አመት በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ሃብት አገኘች ተባለ

አርትስ 29/12/2010
ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተለያዩ አገራት ጋር ባከናወነችው የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ሃብት ማግኘቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሃብቱ ከአሜሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና ኦሺኒያ አገራት እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተገኘ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እያከናወኑት ያለው የፖለቲካ ዲፕሎማሲ አወንታዊ ሚና መጫወቱ ተገልጿል።
በዓመቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በፕሬዝዳንቱ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደረጃ ወደተለያዩ አገራት ጉብኝቶች ተደርገዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ፤ ኢትዮጵያ ከየትኛውም አገር ጋር የምትመሰርተው የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ግንኙነት የሚያተኩረው በምጣኔ ሃብታዊ ትብብር ላይ ነው ይህ እውን እንዲሆን በ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያን የፖለቲካ ዲፕሎማሲ የሚያጠናክሩ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ጉልህ ተጽዕኖ ከሚኖራቸው አገራት ጋር የተፈጠረውን ግንኙነት ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት ማሻገርን ያለሙ ጥናቶች መከናወናቸውንም ለአብነት አንስተዋል።
በ2010 በጀት ዓመት በርካታ ጥናቶች ተካሄደው ከዘጠኝ የተለያዩ አገራት ጋር ስትራቴጃዊ አጋርነት ደረጃ ሊያደርሱን የሚገቡ ጉዳዮች ተለይተው፤እነዚያ ጉዳዮች ውስጥ የተመለከቱት አንኳር ጉዳዮች ወደ ስራ ተቀይረው ስራዎች እየተሰሩ ነው የሚገኙት። እነዚህም አገሮች አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ኩባ፣ ብራዚልና ህንድ ሲሆኑ፤ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለመፍጠር እነዚህን አገራት መርጠን ጥናቶች አካሄደናል ነው ያለው ሚኒስቴር መስሪያቤቱ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *