loading
ኢጋድ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላምና በደህንነት ጉዳዮች ላይ በጋራ ሊሰሩ ነዉ

ኢጋድ እና ተ.መ.ድ. የሚያደርጉትን 2ኛው ከፍተኛ የፖለቲካ የውይይት መድረክ ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ በኒውዮርክ ከሚገኙ የኢጋድ አባል አገራት ተወካዮች ጋር ውጤታማ ውይይት ተደርጓል ተብሏል፡፡

ስብሰባው በታህሳስ ወር መጨረሻ ላይ በዩጋንዳ ካምፓላ የሚካሄድ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች በጋራ በሚሰሩባቸው በተለይም በሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የመጀመሪየው የውይይት መድረክ እ.ኤ.አ. በ2015 በጅቡቲ መካሄዱ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *