ከእስራኤል ጋር ግንኙነት እንፍጠር ያሉት ባለ ስልጣን ከስራቸው ተባረሩ፡፡
ከእስራኤል ጋር ግንኙነት እንፍጠር ያሉት ባለ ስልጣን ከስራቸው ተባረሩ፡፡
በሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት በዳይሬክተርነት ሲያገልግሉ የነበሩት አብዱላሂ ዱል ሀገራቸው ከእስራኤል ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት ብትፈጥር መልካም መሆኑን ትዊተር ገፃቸው በማስፈራቸው ስራቸውን ማጣታቸው ተሰምቷ፡፡
ዳይሬክተሩ ከየትኛውም ሀገር ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት መፍጠር ሰላም እና ትብብርን ያጠናክር እንደሆነ እንጂ ማንንም አይጎዳም ብለዋል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው አብዱላሂ ዱል እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር እስከ መጋቢት 31 ቀን ድረስ በሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ዳይሬክተሩ ለመባረራቸው ምክንያት በሆነው ጽሁፋቸው ፍልስጤሞች የእስራኤል ክፉ ጠላቶች መሆናቸውን ጠቅሰው ጋዛ ውስጥ የራሳቸውን ህዝብ የሚያግቱ እና ሲቪል ሰዎችን የሚገድሉ በማለት ተችተዋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ