loading
ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደመጡበት ሲመለሱ ሽኝት ተደረገላቸው

ባለፈው ዓመት ከኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን ቦረቻ ወረዳ ተፈናቅለው የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆች አካባቢው ሰላም በመሆኑ ወደ መጡበት እንዲመለሱ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አማረ ክንዴ አንደተናገሩት ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ከዞኑ አስተዳደር ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በጉዞ ላይ እና ከደረሱም በኋላ የሚጠቀሙባቸው የምግብ ድጋፍ መዘጋጀቱንም ኃላፊው ተናግረዋል።

መንግሥት የዜጎችን ተዘዋውሮ የመሥራት ሕገ-መንግሥታዊ መብት ማስጠበቅ አንዳለበትም አቶ አህመድ አሳስበዋል ሲል አማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *