loading
ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ የክረምት ዝናብ በተወሰኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተፅዕኖ እንደሚኖረው ተገለጸ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2013  ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ የክረምት ዝናብ በተወሰኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተፅዕኖ እንደሚኖረው ተገለጸ:: የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ የክረምቱ ዝናብ ተፅዕኖ ሊበረታ ስለሚችል በአርሶና አርብቶ አደር አካባቢዎች ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ የክረምት ዝናብ ተፅዕኖው ሊጀምር እንደሚችል የጠቆሙት አቶ አህመዲን፤ በአንዳንድ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በማሳ ላይ ውሃ የመተኛትና ሰብሉን የማበላሸት ተፅዕኖም ሊያደርስ ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል። በአንዳንድ ተፋሰሶች ላይ ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል በመጠቆምም ሁኔታው በአዎንታዊ ጎኑ የወራጅ ውሃ መጠን ስለሚጨምር ለግድቦችና ለውሃ ማቆሪያ ኩሬዎች ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል ሁሉም የወለጋ ዞኖች፣ ጅማ፣ ኢሉ-አባቦራ፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዞኖች፤ በአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብ ጎጃምና የባህር ዳር ዙሪያ፤ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ በሲዳማ ዞኖች ከዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች መጠናከር ጋር ተያይዞ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል ብለዋል። ዝናቡ በአርሶና አርብቶ አደር አካባቢዎች ስለሚጨምር የሚገኘውን ውሃ በአግባቡ መጠቀም ይገባል
ሲሉም መክረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *