loading
ከ90 ዓመታት በኃላ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ሙሉ እድሳት የተደረገለት የነቀምቴ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተሻለ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 ከ90 ዓመታት በኃላ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ሙሉ እድሳት የተደረገለት የነቀምቴ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተሻለ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ::የምስራቅ ወለጋ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ለአርትስ በላከዉ መግለጫ የነቀምቴ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለበርካታ ዓመታት እድሳት ሳይደረግለት የቆየና ለአመታት በብልሹ አሰራርና ለታካሚዎች አመቺ ባለመሆኑ ከህብረተሰቡ በርካታ ቅሬታዎችና ወቀሳዎችን ሲያስተናግድ እንደቆየ ገልጿል፡፡ሆስፒታሉ እድሳት የተደረገለት የሆስፒታሉ ሰራተኞች፣ ውጭ አገር የሚኖሩና የአከባቢው ህብረተሰብ ባደረጉት የገንዘብ፣ የመሳሪያና የተለያዩ ድጋፎች ሲሆን፤ ከ90 ዓመታት በኃላም ለሆስፒታሉ የተለያዩ የእድሳት እና የህክምና መሳሪያ የማሟላት ስራዎች ተሰርተዋል።በተሰራው ስራ ለታካሚም ሆነ ለአስታማሚ ንጹህና ምቹ አከባቢን መፍጠር ተችሏል ያሉት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ታሪኩ ታደሰ የማህበረሰቡ ተሳትፎና ድጋፍ ለዓለም ምሳሌ መሆን የሚችል ተግባር ነው ብለዋል።ለሆስፒታሉ እድሳትና ለመጣው ለውጥ ከፍተኛ ሚናና አስተዋፅኦ ለነበራቸው አካላት የምስጋና ስነስረአት የተካሄደ ሲሆን፤ ለሆስፒታሉ ያደረጉት ድጋፍ ፍሬ አፍርቶ በማየታቸው ወደ ፊትም የሚያደርጉትን ድጋ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም በጎ ፍቃደኞቹ ገልጸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *